وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا عَرَّضْتُم بِهِۦ مِنْ خِطْبَةِ ٱلنِّسَآءِ أَوْ أَكْنَنتُمْ فِىٓ أَنفُسِكُمْ عَلِمَ ٱللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ وَلَٰكِن لَّا تُوَاعِدُوهُنَّ سِرًّا إِلَّآ أَن تَقُولُوا۟ قَوْلًا مَّعْرُوفًا وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy235. (ወንዶች ሆይ!) ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች የጋብቻ (አሽሙር) ፍንጭ በመስጠታችሁ ወይም እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ በውስጣችሁ በማሰባችሁ ምክንያት በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህ እናንተ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱን ሀሳብ እንደምታስተናግዱ ቀድሞውኑ ያውቃል:: ስለዚህ (አሽሙር) ፍንጭ መስጠትንና ማሰብን ፈቀደላችሁ:: ግና በሕግ የታወቀን ጨዋ ንግግር የምትነጋገሩ ካልሆናችሁ በስተቀር የተፃፈው የኢዳ ጊዜው እስከሚደርስ ድረስ ለትዳር እንደምትፈልጓቸው በሚስጥር ቃል አትግቡላቸው:: ጋብቻን ለመዋዋልም ቁርጥ ሀሳብ አታድርጉ:: አላህ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን እወቁ:: ተጠንቀቁም፤ አላህ መሀሪና ታጋሽ መሆኑንም እወቁ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሴቶችንም ከማጨት በርሱ ባሸሞራችሁበት ወይም በነፍሶቻችሁ ውስጥ (ለማግባት) በደበቃችሁት በናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ አላህ እናንተ በእርግጥ የምታስታውሷቸው መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ (ስለዚህ ማሸሞርንና ማሰብን ፈቀደላችሁ፡፡) ግን በሕግ የታወቀን ንግግር የምትነጋገሩ ካልኾናችሁ በስተቀር፤ ምስጢርን (ጋብቻን) አትቃጠሩዋቸው፡፡ የተጻፈውም (ዒዳህ) ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ ሐሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ፡፡