caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 128

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:128

رَبَّنَا وَٱجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَآ أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَآ إِنَّكَ أَنتَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy128. «ጌታችን ሆይ! ላንተው ፍጹም ታዛዦችም አድርገን:: ከዘሮቻችንም ላንተ ፍጹም ታዛዦች ሕዝቦችን አስነሳ:: አምልኳዊ ክንውኖቻችንንም አሳውቀን:: ንሰሀችንን ተቀበለን:: ጸጸትን ተቀባይና ሩህሩህ አንተ ብቻ ነህና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ጌታችን ሆይ! ላነተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዦች ሕዝቦችን (አድርግ)፡፡ ሕግጋታችንንም አሳየን፤ (አሳውቀን)፡፡ በኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70