caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 255

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:255

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْحَىُّ ٱلْقَيُّومُ لَا تَأْخُذُهُۥ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ مَن ذَا ٱلَّذِى يَشْفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذْنِهِۦ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفْظُهُمَا وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy255. አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ምንግዜም ሕያው፤ በራሱ የተብቃቃ ነው:: ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ አትይዘዉም:: በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው? (ከፍጡራን) ሁሉ በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል:: በሻው ነገር እንጂ ከእውቀቱ (ፍጡራን) በምንም ነገር አያካብቡም:: መንበሩ የሰማያትንና የምድርን ስፋት ይበልጣል:: ጥበቃቸዉም አያቅተዉም:: እርሱ የሁሉ የበላይና ታላቅ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡ {1}
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70