وَقَالُوا۟ لَن تَمَسَّنَا ٱلنَّارُ إِلَّآ أَيَّامًا مَّعْدُودَةً قُلْ أَتَّخَذْتُمْ عِندَ ٱللَّهِ عَهْدًا فَلَن يُخْلِفَ ٱللَّهُ عَهْدَهُۥٓ أَمْ تَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy80. (አይሁዶች) “የገሀነም እሳት ለተቆጠሩ ውስን ቀናት ብቻ እንጂ ፈጽሞ አትነካንም” አሉ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) “በዚህ ጉዳይ ከአላህ ዘንድ ቃል ኪዳን ይዛችኋልን? ይህ ከሆነ አላህም ኪዳኑን አያፈርስም:: ወይስ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?” በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እሳትም የተቆጠሩን ቀኖች እንጂ አትነካንም» አሉ፡፡ «አላህ ዘንድ ቃል ኪዳን ይዛችኋልን? (ይህ ከኾነ) አላህም ኪዳኑን አያፈርስም፤ በእውነቱ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁ» በላቸው፡፡