caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 229

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:229

ٱلطَّلَٰقُ مَرَّتَانِ فَإِمْسَاكٌۢ بِمَعْرُوفٍ أَوْ تَسْرِيحٌۢ بِإِحْسَٰنٍ وَلَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَأْخُذُوا۟ مِمَّآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ شَيْـًٔا إِلَّآ أَن يَخَافَآ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا يُقِيمَا حُدُودَ ٱللَّهِ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا فِيمَا ٱفْتَدَتْ بِهِۦ تِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ فَلَا تَعْتَدُوهَا وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy229. የመመለስ እድል የሚሰጠው ፍቺ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው:: ከዚያም በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው:: (ባሎች ሆይ!) የአላህን ህግጋት ያለማክበር ስጋት ካልኖረባቸው በስተቀር ከሰጣችኋቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ አይፈቀድላችሁም:: የአላህን ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብትገነዘቡ ነፃ ለማውጣት በምትፈጽመው ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: እኒህ የአላህ ሕግጋት ናቸው:: አትተላለፏቸው:: እነዚያ እነርሱ የአላህን ሕግጋት የሚተላለፉ ሁሉ (በደለኞች) አጥፊዎች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqፍች ሁለት ጊዜ ነው፤ (ከዚህ በኋላ) በመልካም መያዝ ወይም በበጎ አኳኋን ማሰናበት ነው፡፡ የአላህንም ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ካላወቁ በስተቀር ከሰጣችኃቸው ነገር ምንንም ልትወስዱ ለእናንተ (ለባሎች) አይፈቀድላችሁም፡፡ የአላህንም ሕግጋት አለመጠበቃቸውን ብታውቁ በእርሱ (ነፍሷን) በተበዠችበት ነገር በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለም፡፡ ይህች የአላህ ሕግጋት ናት፤ አትተላለፏትም፡፡ የአላህንም ሕግጋት የሚተላለፉ እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70