وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَٰقَ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ لَا تَعْبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَانًا وَذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَقُولُوا۟ لِلنَّاسِ حُسْنًا وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ ثُمَّ تَوَلَّيْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا مِّنكُمْ وَأَنتُم مُّعْرِضُونَ
Amharic Translation - Africa Academy83. (የኢስራኢል-ልጆችን) “አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ:: ለወላጆችም በጎን ስራ ስሩ:: ለዝምድና ባለቤቶች፤ ለየቲሞችና ለሚስኪኖችም በጎን ዋሉ:: ለሰዎችም ሁሉ መልካምን ብቻ ተናገሩ :: ሶላትን ደንቡን ጠብቃች ስገዱ:: ዘካን ለተገቢው ስጡ” በማለት ጥብቅ ቃልኪዳን በያዝንባቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ):: ከዚያም ከእናንተ ጥቂቶቹ ሲቀሩ ሸሻችሁ:: እናንተ (ቃልኪዳንንም) የምትተው ናችሁ፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ በወላጆችም በጎን ሥራ (አድርጉ)፤ በዝምድና ባለቤቶችም፣ በየቲሞችም (አባት የሌላቸው ልጆች) በምስኪኖችም (በጎ ዋሉ)፤ ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ በማለት በያዝንባቸው ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ከዚያም ከናንተ ጥቂቶች ሲቀሩ ሸሻችሁ እናንተም (ኪዳንን) የምትተዉ ናችሁ፡፡