أَيَوَدُّ أَحَدُكُمْ أَن تَكُونَ لَهُۥ جَنَّةٌ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعْنَابٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ لَهُۥ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَأَصَابَهُ ٱلْكِبَرُ وَلَهُۥ ذُرِّيَّةٌ ضُعَفَآءُ فَأَصَابَهَآ إِعْصَارٌ فِيهِ نَارٌ فَٱحْتَرَقَتْ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy266. ከናንተ አንዳችሁ ሁሉን ዓይነት ምርት የምትሰጥ ከስሯ ወንዞች የምፈሱባት የዘንባባዎችና የወይኖች የአትክልት ቦታ ልትኖረው እርጅናም ሊነካውና በእነርሱም ደካሞች ረዳት የለሽ ህፃናት ያሉት ሲሆኑ በውስጡ እሳት ያለበት ውርጭ ምርቱ ላይ አደጋ ሊያደርስበት እና ልትቃጠልበት ይወዳልን? ልክ እንደዚሁ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል:: ልታስተነትኑ ይከጀላልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(ከእናንተ) አንዳችሁ ለርሱ ከዘምባባና ከወይኖች በስርዋ ወንዞች የሚፈሱባት አትክልት ልትኖረው፣ በውስጧም ለርሱ ከየፍሬው ሁሉ ሊኖረው እርጅናም ሊነካውና ለርሱ ደካማዎች ዝርያዎች ያሉት ሲኾን በውስጡ እሳት ያለበት ውርጭ ሊያገኛትና ልትቃጠል ይወዳልን እንደዚሁ አላህ አንቀጾችን ለእናንተ ያብራራል፤ ልታስተነትኑ ይከጀላልና፡፡