لَّيْسَ عَلَيْكَ هُدَىٰهُمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَهْدِى مَن يَشَآءُ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَلِأَنفُسِكُمْ وَمَا تُنفِقُونَ إِلَّا ٱبْتِغَآءَ وَجْهِ ٱللَّهِ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِنْ خَيْرٍ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ
Amharic Translation - Africa Academy272. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ማቅናት ባንተ ላይ ግዴታ የለብህም:: አላህ ግን የሚሻውን ሰው ያቀናል:: የምትለግሱት ገንዘብ ሁሉ ምንዳው ለነፍሶቻችሁ ብቻ ነው:: የአላህን ውዴታውን በመፈለግ እንጂ ምንንም አትለግሱ:: ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ ምንዳው ወደ እናንተ ይሞላል:: እናንተም ቅንጣት ያህል አትበደሉም፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነርሱን ማቅናት በአንተ ላይ የለብህም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል፡፡ ከገንዘብም የምትለግሱት (ምንዳው) ለነፍሶቻችሁ ነው፡፡ የአላህንም ፊት (ውዴታውን) ለመፈለግ እንጂ አትለግሱም፡፡ ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ (ምንዳው) ወደናንተ ይሞላል፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡