caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 273

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:273

لِلْفُقَرَآءِ ٱلَّذِينَ أُحْصِرُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا يَسْتَطِيعُونَ ضَرْبًا فِى ٱلْأَرْضِ يَحْسَبُهُمُ ٱلْجَاهِلُ أَغْنِيَآءَ مِنَ ٱلتَّعَفُّفِ تَعْرِفُهُم بِسِيمَٰهُمْ لَا يَسْـَٔلُونَ ٱلنَّاسَ إِلْحَافًا وَمَا تُنفِقُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy273. (ምጽዋት የምትሰጡት ዘካና ልገሳ) ለእነዚያ በአላህ መንገድ በግል ሕይወታቸው ከመንቀሳቀስ (ለታገዱት) ፋታ ላጡ ድሆች ነው:: መሬት ውስጥ መጓዝ (ልመና) አይችሉም:: ከቁጥብነታቸው የተነሳ ውስጣቸውን የማያውቅ ሰው ሁሉ ሀብታሞች ናቸው ብሎ ይገምታቸዋል:: በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ:: ሰዎችን በችክታ አይለምኑም:: ከገንዘብም የምትለግሱትን ሁሉ አላህ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(የምትመጸውቱት) ለእነዚያ በአላህ መንገድ (ለመታገል ሲሉ) ለታገዱት ድኾች ነው፡፡ በምድር መኼድን አይችሉም፡፡ (ልመናን) ከመጥጠበቃቸው (የተነሳ) የማያውቅ ሰው ሀብታሞች ናቸው ብሎ ይጠረጥራቸዋል፡፡ በምልክታቸው ታውቃቸዋለህ፡፡ ሰዎችን በችክታ አይለምኑም፡፡ ከገንዘብም የምትለግሱት አላህ እርሱን ዐዋቂ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70