وَلَئِنْ أَتَيْتَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ بِكُلِّ ءَايَةٍ مَّا تَبِعُوا۟ قِبْلَتَكَ وَمَآ أَنتَ بِتَابِعٍ قِبْلَتَهُمْ وَمَا بَعْضُهُم بِتَابِعٍ قِبْلَةَ بَعْضٍ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم مِّنۢ بَعْدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ إِنَّكَ إِذًا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy145.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያ መጽሐፍን ለተሰጡት ሕዝቦች የምትችለውን ያህል ተዓምር (መረጃ) ሁሉ ብታቀርብላቸው እንኳ ቂብላህን አይከተሉም:: አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም:: ከፊላቸዉም የከፊሉን ቂብላ አይከተሉም:: ከእውቀትም (ራእይ) ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ያን ጊዜ አንተ ከአጥፊዎች ትሆናለህ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያንም መጽሐፍን የተሰጡትን በአስረጅ ሁሉ ብትመጣቸው ቂብላህን አይከተሉም፡፡ አንተም ቂብላቸውን ተከታይ አይደለህም፡፡ ከፊላቸውም የከፊሉን ቂብላ ተከታይ አይደሉም፡፡ ከዕውቀትም (ከራዕይ) ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተ ያን ጊዜ ከበዳዮች ነህ፡፡