مَثَلُهُمْ كَمَثَلِ ٱلَّذِى ٱسْتَوْقَدَ نَارًا فَلَمَّآ أَضَآءَتْ مَا حَوْلَهُۥ ذَهَبَ ٱللَّهُ بِنُورِهِمْ وَتَرَكَهُمْ فِى ظُلُمَٰتٍ لَّا يُبْصِرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy17. የእነርሱ ንፍቅና ምሳሌ ልክ እንደዚያ እሳትን እንዳነደደና ከዚያ በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራችለት ጊዜ አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው እና በጨለማዎች ውስጥ የማያዩ ሆነው እንደተዋቸው ብጤ ነው፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(በንፍቅና) ምሳሌያቸው እንደዚያ እሳትን እንዳነደደ ሰው በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራች ጊዜም አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው በጨለማዎችም ውስጥ የማያዩ ኾነው እንደተዋቸው (ሰዎች) ብጤ ነው፡፡