caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 25

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:25

وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ كُلَّمَا رُزِقُوا۟ مِنْهَا مِن ثَمَرَةٍ رِّزْقًا قَالُوا۟ هَٰذَا ٱلَّذِى رُزِقْنَا مِن قَبْلُ وَأُتُوا۟ بِهِۦ مُتَشَٰبِهًا وَلَهُمْ فِيهَآ أَزْوَٰجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَهُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑትንና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መሆኑን አብስራቸው:: በእርሷም ፍራፍሬ በተለገሱ ቁጥር (ፍሬዎቿ ስለሚመሳሰሉ) «ይህማ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው።» ይላሉ:: (እርሱ ተመሳሳይ ሆኖ ይሰጣቸዋል) ለእነርሱም በውስጧ ንጹህ ሚስቶች አሏቸው:: እነርሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡ ከርሷ ከፍሬ (ዓይነት) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር (ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ) «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት፡፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው፡፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70