caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 126

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:126

وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ رَبِّ ٱجْعَلْ هَٰذَا بَلَدًا ءَامِنًا وَٱرْزُقْ أَهْلَهُۥ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ مَنْ ءَامَنَ مِنْهُم بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ قَالَ وَمَن كَفَرَ فَأُمَتِّعُهُۥ قَلِيلًا ثُمَّ أَضْطَرُّهُۥٓ إِلَىٰ عَذَابِ ٱلنَّارِ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy126. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ይህንን ሀገር (መካን) ሰላማዊ ሀገር አድርገው:: ከኗሪዉም መካከል በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ክፍል ከፍራፍሬዎች ሲሳይ ስጠው።» ባለ ጊዜ (የነበረውን ታሪክ አስታውስ):: አላህም «የካደውንም በጥቂቱ እንዲጎናጸፍ አደርገዋለሁ:: ከዚያ ወደ እሳት ቅጣት እዳርገዋለሁ:: ይህም እጅግ አስከፊ መመለሻ ነው።» አለ
Amharic Translation - Muhammad Sadiqኢብራሂም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ጌታዬ ሆይ! ይህንን ጸጥተኛ አገር አድርግ፡፡ ቤተሰቦቹንም ከነሱ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነውን ሰው ከፍሬዎች ስጠው፡፡ (አላህም) የካደውንም ሰው፤ (እሰጠዋለሁ)፡፡ ጥቂትም እጠቅመዋለሁ፤ ከዚያም ወደ እሳት ቅጣት አስጠጋዋለሁ፤ ምን ትከፋም መመለሻ! (አለ)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70