caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 264

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:264

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُبْطِلُوا۟ صَدَقَٰتِكُم بِٱلْمَنِّ وَٱلْأَذَىٰ كَٱلَّذِى يُنفِقُ مَالَهُۥ رِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ صَفْوَانٍ عَلَيْهِ تُرَابٌ فَأَصَابَهُۥ وَابِلٌ فَتَرَكَهُۥ صَلْدًا لَّا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَىْءٍ مِّمَّا كَسَبُوا۟ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy264. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ገንዘብን ለሰዎች ለማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻው ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመፃደቅና ተረጂውን በማስከፋት አታበላሹ:: የዚህ አይነቱም ድርጊት ምሳሌው በላዩ ላይ አፈር እንዳረፈበት ለስላሳ ድንጋይ ሲሆን እሱም ሀይለኛ ዝናብ አግኝቶት እንደተራቆተ ብጤ ነው:: እነኝህ አይነት ሰዎች ከሰሩት ነገር በምኑም ሊጠቀሙ አይችሉም:: አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን በፍጹም ወደ ቀናው መንገድ አይመራምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅና በማስከፋት አታበላሹ፡፡ ምሳሌውም በላዩ ዐፈር እንዳለበት ለንጣ ድንጋይ ኃይለኛ ዝናብ እንዳገኘውና ምልጥ አድርጎ እንደተወው ብጤ ነው፡፡ ከሠሩት ነገር በምንም ላይ (ሊጠቀሙ) አይችሉም፡፡ አላህ ከሓዲያንን ሕዝቦች አይመራም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70