أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِى حَآجَّ إِبْرَٰهِـۧمَ فِى رَبِّهِۦٓ أَنْ ءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ ٱلْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ رَبِّىَ ٱلَّذِى يُحْىِۦ وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا۠ أُحْىِۦ وَأُمِيتُ قَالَ إِبْرَٰهِـۧمُ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَأْتِى بِٱلشَّمْسِ مِنَ ٱلْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ ٱلْمَغْرِبِ فَبُهِتَ ٱلَّذِى كَفَرَ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy258. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን አላህ ንግስናን ስለ ሰጠውና በጌታው ጉዳይ በኢብራሂም ላይ ክርክር ስለ ከፈተው ሰው (ታሪክ) መረጃ አላየህምን? ኢብራሂም፡-‹‹ጌታዬ ያ የፈለገውን ሕያው የሚያደርግና የፈለገውን የሚገድል ነው›› ሲለው «እኔም የፈለኩትን ህያው አደርጋለሁ፤ የፈለኩትን እገድላለሁ» አለ:: ኢብራሂምም፡- «አላህ ጸሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣል:: እስኪ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው:: ያም የካደ ሰው ዋለለ (መልስ አጣ):: አላህ ግፈኛ ሕዝቦችን ሁሉ አይመራምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደዚያ አላህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ እገድላለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አላህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል (አንተ) ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ፤ (መልስ አጣ) አላህ በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡