لَّيْسَ ٱلْبِرَّ أَن تُوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ قِبَلَ ٱلْمَشْرِقِ وَٱلْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ ٱلْبِرَّ مَنْ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلْكِتَٰبِ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ وَءَاتَى ٱلْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ ذَوِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينَ وَٱبْنَ ٱلسَّبِيلِ وَٱلسَّآئِلِينَ وَفِى ٱلرِّقَابِ وَأَقَامَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَى ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَٰهَدُوا۟ وَٱلصَّٰبِرِينَ فِى ٱلْبَأْسَآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَحِينَ ٱلْبَأْسِ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ صَدَقُوا۟ وَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُتَّقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy177. መልካምነት ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞራችሁ አይደለም። መልካምነት በአላህ፣ በመጨረሻው ቀን፣ በመላዕክት፣ በመጸሐፍት በነብያት ያመነ፤ ገንዘብንም ምንም ያህል የነዋይ (ገንዘብ) ፍቅር ቢኖረዉም ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለሚስኪኖች፣ ለመንገደኞች፣ ለለማኞች፣ ባሪያዎችን ነፃ ለማውጣት የሰጠ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ የሰገደና ዘካንም ያወጣ ነው:: እንዲሁም ቃልኪዳን በገቡ ጊዜም ቃልኪዳናቸውን የሚሞሉ በችግር፣ በበሽታና በፍልሚያ ጊዜ ታጋሾች ናቸው። እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል:: አላህን የሚፈሩም ናቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው፤ ገንዘብንም ከመውደዱ ጋር ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኞችም፣ ለለማኞችም፣ ለጫንቃዎችም (ማስለቀቅ) የሰጠ ሰውና፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቆ የሰገደ፣ ዘካንም የሰጠ፤ ቃል ኪዳንም በገቡ ጊዜ በኪዳናቸው የሞሉ (ሰዎች ሥራ) ነው፡፡ በችግር በበሽታና በጦር ጊዜም ታጋሾችን (እናወድሳለን)፡፡ እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ ናቸው፡፡ እነዚያም ተጠንቃቂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡