أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ خَرَجُوا۟ مِن دِيَٰرِهِمْ وَهُمْ أُلُوفٌ حَذَرَ ٱلْمَوْتِ فَقَالَ لَهُمُ ٱللَّهُ مُوتُوا۟ ثُمَّ أَحْيَٰهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy243. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብዙ ሺህ ሆነው ሞትን በመፍራት ከሀገሮቻቸው የወጡ ሰዎችን ታሪክ አላየህምን (አላወክምን?) አላህ ለእነርሱ «ሙቱ» አላቸው:: ሞቱም:: ከዚያ እንደገና ነፍስ ዘራባቸው:: አላህም ለሰዎች እጅግ ቸር ነው:: ይሁንና አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ እነዚያ እነርሱ ብዙ ሺሕ ኾነው ሞትን ለመፍራት ከሀገሮቻቸው ወደ ወጡት ሰዎች ዕውቀትህ አልደረሰምን? አላህም ለነርሱ «ሙቱ» አላቸው፤ (ሞቱም)፡፡ ከዚያም ሕያው አደረጋቸው፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ባለችሮታ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡