وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمُ ٱبْتِغَآءَ مَرْضَاتِ ٱللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍۭ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَـَٔاتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy265. የእነዚያ የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ከነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ብለው ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱት ምሳሌያቸው በተስተካከለች ከፍተኛ ቦታ ላይ እንዳለች አትክልት ሲሆን ይህች አትክልት ከፍተኛ ዝናብ አግኝታ እጥፍ ድርብ ምርት እንደሰጠች ከፍተኛ ዝናብ ባታገኝ እንኳን ካፊያ ብቻ እንደሚበቃት የአትክልት አይነት ይመስላል:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ለነፍሶቻቸው (እምነትን) ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡