caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 54

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:54

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ إِنَّكُمْ ظَلَمْتُمْ أَنفُسَكُم بِٱتِّخَاذِكُمُ ٱلْعِجْلَ فَتُوبُوٓا۟ إِلَىٰ بَارِئِكُمْ فَٱقْتُلُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ عِندَ بَارِئِكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy54. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለም ጊዜ የዋልነውን ውለታ አስታውሱ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን አምላክ በማድረጋችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ:: በመሆኑም ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ:: ከመካከላችሁ ወንጀለኛ ወገኖቻችሁን ግደሉ:: ይሃችሁ ድርጊት በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለእንናተ በላጭ ነው። በእናንተም ላይ ምህረቱን አወረደ:: እነሆ እርሱ (አላህ) ጸጸትን ተቀባይ ምህረተኛ አዛኝ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን (አምላክ አድርጋችሁ) በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ፡፡ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ፤ ይሃችሁ በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለናንተ በላጭ ነው» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70