وَأَتِمُّوا۟ ٱلْحَجَّ وَٱلْعُمْرَةَ لِلَّهِ فَإِنْ أُحْصِرْتُمْ فَمَا ٱسْتَيْسَرَ مِنَ ٱلْهَدْىِ وَلَا تَحْلِقُوا۟ رُءُوسَكُمْ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْهَدْىُ مَحِلَّهُۥ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوْ بِهِۦٓ أَذًى مِّن رَّأْسِهِۦ فَفِدْيَةٌ مِّن صِيَامٍ أَوْ صَدَقَةٍ أَوْ نُسُكٍ فَإِذَآ أَمِنتُمْ فَمَن تَمَتَّعَ بِٱلْعُمْرَةِ إِلَى ٱلْحَجِّ فَمَا ٱسْتَيْسَرَ مِنَ ٱلْهَدْىِ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍ فِى ٱلْحَجِّ وَسَبْعَةٍ إِذَا رَجَعْتُمْ تِلْكَ عَشَرَةٌ كَامِلَةٌ ذَٰلِكَ لِمَن لَّمْ يَكُنْ أَهْلُهُۥ حَاضِرِى ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
Amharic Translation - Africa Academy196. ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈጽሙ:: ከጀመራችሁ በኋላ ብትታጉዱም ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ:: መስዋእቱ ከመታረጃው ስፍራ እስኪደርስ ድረስም ራሶቻችሁን አትላጩ:: ከናንተም ውስጥ በሐጅ ላይ ሁኖ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከመፆም ወይም መስዋዕትን ቤዛ መስጠት አለበት:: ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈጸሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈጸም የተገላገለ ሰው ከመስዋእቱ የተገራውን (የቻለዉን) መሰዋት አለበት:: ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀናት በሐጅ (ወራት) ላይ ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት:: እነዚህ ሙሉ አስር (ቀናት) ናቸው:: ይህም (ህግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው:: አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ መሆኑንም እወቁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሐጅንና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ፡፡ ብትታገዱም ከሀድይ (ከመሥዋእት) የተገራውን (መሰዋት) አለባችሁ፡፡ ሀድዩም እስፍራው እስከሚደርስ ድረስ ራሶቻችሁን አትላጩ፡፡ ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በራሱ ሁከት ያለበት የኾነ ሰው (ቢላጭ) ከጾም ወይም ከምጽዋት ወይም ከመሥዋዕት ቤዛ አለበት፡፡ ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ በዑምራ የተጣቀመ ሰው ከሀድይ የተገራውን (መሠዋት) አለበት፡፡ ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀኖች በሐጅ ወራት፤ ሰባትም በተመለሳችሁ ጊዜ መጾም አለበት፡፡ ይህች ሙሉ ዐሥር (ቀናት) ናት፡፡ ይህም (ሕግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልኾኑ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ቅጣተ ብርቱ መኾኑን እወቁ፡፡