وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ لَوْلَا يُكَلِّمُنَا ٱللَّهُ أَوْ تَأْتِينَآ ءَايَةٌ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِم مِّثْلَ قَوْلِهِمْ تَشَٰبَهَتْ قُلُوبُهُمْ قَدْ بَيَّنَّا ٱلْـَٔايَٰتِ لِقَوْمٍ يُوقِنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy118. እነዚያ የማያውቁት «(አንተ መልዕክተኛ ስለመሆንህ) አላህ ለምን አያናግረንም? ወይም (ለእውነተኛነትህ) ተዓምር አይመጣልንም ኖሯልን? አሉ:: እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚሁ ንግግራቸው ብጤ ብለዋል:: ልቦቻቸው በክህደት ተመሳሰሉ:: ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን በእርግጥ አብራርተናል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም የማያውቁት (አንተ መልክተኛ ስለመኾንህ) አላህ አያናግረንም ኖሮአልን? ወይም (ለእውነተኛነትህ) ታምር አትመጣልንም ኖሮአልን? አሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከነሱ በፊት የነበሩት እንደ ንግግራቸው ብጤ ብለዋል፡፡ ልቦቻቸው (በክሕደት) ተመሳሰሉ፡፡ ለሚያረጋግጡ ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ አብራርተናል፡፡