ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ثُمَّ لَا يُتْبِعُونَ مَآ أَنفَقُوا۟ مَنًّا وَلَآ أَذًى لَّهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
Amharic Translation - Africa Academy262. እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ከዚያ በሰጡት ነገር መመፃደቅና ማስከፋት የማያስከትሉ ሁሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አለላቸው:: በእነርሱም ላይ ስጋትም የለባቸዉም። አይተክዙምም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ከዚያም የሰጡትን ነገር መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፡፡