بِئْسَمَا ٱشْتَرَوْا۟ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمْ أَن يَكْفُرُوا۟ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ فَبَآءُو بِغَضَبٍ عَلَىٰ غَضَبٍ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ مُّهِينٌ
Amharic Translation - Africa Academy90. ነፍሶቻቸውን የሸጡበት (የለወጡበት) ነገር ከፋ! ይኸዉም አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ችሮታውን ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው:: እናም የአላህን ቁጣ በተደጋጋሚ አትርፈዋል:: ለካሐዲያንም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqነፍሶቻቸውን በርሱ የሸጡበት ነገር ከፋ! (እርሱም) አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው (ራእይን) ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡ በቁጣ ላይም ቁጣ (የተረጋገጠባቸው ሲኾኑ) ተመለሱ፡፡ ለከሓዲዎችም አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡