caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 228

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:228

وَٱلْمُطَلَّقَٰتُ يَتَرَبَّصْنَ بِأَنفُسِهِنَّ ثَلَٰثَةَ قُرُوٓءٍ وَلَا يَحِلُّ لَهُنَّ أَن يَكْتُمْنَ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِىٓ أَرْحَامِهِنَّ إِن كُنَّ يُؤْمِنَّ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَبُعُولَتُهُنَّ أَحَقُّ بِرَدِّهِنَّ فِى ذَٰلِكَ إِنْ أَرَادُوٓا۟ إِصْلَٰحًا وَلَهُنَّ مِثْلُ ٱلَّذِى عَلَيْهِنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ وَلِلرِّجَالِ عَلَيْهِنَّ دَرَجَةٌ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy228. የተፈቱ ሴቶችም በራሳቸው ሶስትን የወር አበባ ይጠብቁ። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ከሆኑ አላህ በማህጸኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ጽንስ ሊደብቁ አይፈቀድላቸዉም:: ባሎቻቸዉም እርቅን ከፈለጉ በእነዚህ ወራት ውስጥ የመመለስ መብታቸው ቅድሚያ ነው:: ለሴቶች ግዳጅ እንዳለባቸው ሁሉ ፍትሀዊ መብትም አላቸው:: ይሁንና ወንዶች (የበለጠ ሀላፊነትን ስለሚሸከሙ) ብልጫ አላቸው። (ተጥሎባቸዋል):: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁርእ ይጠብቁ፡፡ በአላህና በመጨረሻውም ቀን የሚያምኑ ቢኾኑ አላህ በማሕፀኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ሊደብቁ ለነርሱ አይፈቀድላቸውም፡፡ ባሎቻቸውም በዚህ ውስጥ እርቅን ቢፈልጉ በመማለሳቸው ተገቢዎች ናቸው፡፡ ለእነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በእነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኑዋኑዋር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡ ለወንዶችም (ጣጣቸውን ስለሚሸከሙ) በእነሱ ላይ ብልጫ አላቸው፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70