قَالُوا۟ ٱدْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِىَ قَالَ إِنَّهُۥ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌۢ بَيْنَ ذَٰلِكَ فَٱفْعَلُوا۟ مَا تُؤْمَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy68. እነርሱም «እስቲ ጌታህን ጠይቅልን:: እርሷ ምን እንደሆነች (እድሜዋን) ያብራራልን ዘንድ» አሉ:: እርሱም «‹እርሷ በውልም ያላረጀች ጥጃም ያልሆነች በዚህ መካከል ልከኛ የሆነች ጊደር ናት።› ይላችኋል። የታዘዛችሁትንም ስሩ።» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች (ዕድሜዋን) ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል፤ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡