وَٱلْوَٰلِدَٰتُ يُرْضِعْنَ أَوْلَٰدَهُنَّ حَوْلَيْنِ كَامِلَيْنِ لِمَنْ أَرَادَ أَن يُتِمَّ ٱلرَّضَاعَةَ وَعَلَى ٱلْمَوْلُودِ لَهُۥ رِزْقُهُنَّ وَكِسْوَتُهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ لَا تُكَلَّفُ نَفْسٌ إِلَّا وُسْعَهَا لَا تُضَآرَّ وَٰلِدَةٌۢ بِوَلَدِهَا وَلَا مَوْلُودٌ لَّهُۥ بِوَلَدِهِۦ وَعَلَى ٱلْوَارِثِ مِثْلُ ذَٰلِكَ فَإِنْ أَرَادَا فِصَالًا عَن تَرَاضٍ مِّنْهُمَا وَتَشَاوُرٍ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا وَإِنْ أَرَدتُّمْ أَن تَسْتَرْضِعُوٓا۟ أَوْلَٰدَكُمْ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِذَا سَلَّمْتُم مَّآ ءَاتَيْتُم بِٱلْمَعْرُوفِ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy233. እናቶች ልጆቻቸውን ሁለት ሙሉ ዓመታትን ያጠባሉ:: ይህም ማጥባትን የተሟላ ለማድረግ ለፈለገ ሰው ነው:: በአባት ላይ ምግባቸውንና ልብሳቸውን የማቅረብ ግዴታ አለበት:: ማንም ነፍስ ከችሎታዋ በላይ አትገደድምና:: እናት በልጇ ምክኒያት ጉዳት እንዲደርስባት አይደረግም:: አባትም በልጁ ምክንያት እንዲንገላታ መሆን የለበትም:: በወራሽም ላይ የዚሁ ተመሳሳይ ሀላፊነት አለበት:: ወላጆቹ በመልካም ፈቃድ ልጁን ከጡት መነጠል (ማስጣል) ቢፈልጉ በሁለቱም መማከር በሁለቱም ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: ለልጆቻችሁ አጥቢዎችን ብትቀጥሩ ተስፋ የሰጣችሁትን ክፍያ በአግባቡ እስከሰጣችሁ ድረስ በማስጠባታችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: አላህን ፍሩ:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች መሆኑን እወቁ፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናቶችም ልጆቻቸውን ሙሉ የኾኑን ሁለት ዓመታት ያጥቡ፡፡ (ይህም) ማጥባትን መሙላት ለሻ ሰው ነው፡፡ ለእርሱም በተወለደለት (አባት) ላይ ምግባቸውና ልብሳቸው በችሎታው ልክ አለበት፡፡ ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አትገደድም፡፡ ወላጂት (እናት) በልጅዋ ምክንያት ለርሱ የተወለደለትም (አባት) በልጁ ምክንያት አይጎዳዱ፡፡ በወራሽም ላይ እንደዚሁ ብጤ አለበት፡፡ (ወላጆቹ) ከሁለቱም በኾነ መዋደድና መመካከር (ልጁን ከጡት) መነጠልን ቢፈልጉ በሁለቱም ላይ ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ ልጆቻችሁንም ለሌሎች አጥቢዎች ማስጠባትን ብትፈልጉ ልትሰጡ የሻችሁትን በመልካም ኹኔታ በሰጣችሁ ጊዜ (በማስጠባታችሁ) በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች መኾኑን ዕወቁ፡፡