وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تَذْبَحُوا۟ بَقَرَةً قَالُوٓا۟ أَتَتَّخِذُنَا هُزُوًا قَالَ أَعُوذُ بِٱللَّهِ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْجَٰهِلِينَ
Amharic Translation - Africa Academy67. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለህዝቦቹ «አላህ ላም እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለም ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እነርሱም ለሙሳ «መሳለቂያ ታደርገናለህን?» አሉት። እሱም «ከተሳላቂዎች ከመሆን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለ ጊዜ (አስታወሱ)፡፡«መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህን?» አሉት፡፡ «ከተሳላቂዎች ከመኾን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው፡፡