إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَسْتَحْىِۦٓ أَن يَضْرِبَ مَثَلًا مَّا بَعُوضَةً فَمَا فَوْقَهَا فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّهِمْ وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَيَقُولُونَ مَاذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِهَٰذَا مَثَلًا يُضِلُّ بِهِۦ كَثِيرًا وَيَهْدِى بِهِۦ كَثِيرًا وَمَا يُضِلُّ بِهِۦٓ إِلَّا ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy26. አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝም ትሁን ከሷም በላይ የሆነን ነገር ምሳሌ ከማድረግ አያፍርም። እነዚያማ ያመኑት ምሳሌው ከጌታቸው የተነገረ እውነት መሆኑን ያውቃሉ:: እነዚያ የካዱ ግን «አላህ በዚህ አባባል ምንን ምሳሌ ፈልጎበት ነው?» ይላሉ:: አላህ በምሳሌው ብዙዎችን ያሳስታል:: በእርሱም ብዙዎችን ያቀናል:: በእርሱም አመጸኞችን እንጂ ሌላን አያሳስትም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ (በትንሽነት ወይም በትልቅነት) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡ እነዚያ ያመኑትማ፤ እርሱ (ምሳሌው) ከጌታቸው (የተገኘ) እውነት መኾኑን ያውቃሉ፡፡ እነዚያም የካዱትማ «አላህ በዚህ ምንን ምሳሌ ሻ» ይላሉ፡፡ በርሱ (በምሳሌው) ብዙዎችን ያሳስታል በርሱም ብዙዎችን ያቀናል፡፡ በርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያሳስትም፡፡