caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 198

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:198

لَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَن تَبْتَغُوا۟ فَضْلًا مِّن رَّبِّكُمْ فَإِذَآ أَفَضْتُم مِّنْ عَرَفَٰتٍ فَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ عِندَ ٱلْمَشْعَرِ ٱلْحَرَامِ وَٱذْكُرُوهُ كَمَا هَدَىٰكُمْ وَإِن كُنتُم مِّن قَبْلِهِۦ لَمِنَ ٱلضَّآلِّينَ

Amharic Translation - Africa Academy198. በሐጅ ጊዜ (በስራ) ከጌታችሁ ችሮታን በመፈለጋችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ከአረፋት በተንቀሳቀሳችሁም ጊዜ መሸዐረል ሀራም ዘንድ ስትደርሱ አላህን አውሱ:: ወደ ቀናው የኢስላም መንገድ ስለመራችሁም አውሱት:: ቀደም ሲል በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(በሐጅ ጊዜ በንግድ ሥራ) ከጌታችሁ ትርፍን በመፈለጋችሁ በናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም፡፡ ከዐረፋትም በጎረፋችሁ ጊዜ መሸዐረልሐራም ዘንድ አላህን አውሱ፡፡ (ለሐጅ) ስለመራችሁም አውሱት፡፡ ከመምራቱ በፊትም በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70