caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 89

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:89

وَلَمَّا جَآءَهُمْ كِتَٰبٌ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ مُصَدِّقٌ لِّمَا مَعَهُمْ وَكَانُوا۟ مِن قَبْلُ يَسْتَفْتِحُونَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَلَمَّا جَآءَهُم مَّا عَرَفُوا۟ كَفَرُوا۟ بِهِۦ فَلَعْنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلْكَٰفِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy89. ከእነርሱ ጋር ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ የሆነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከመምጣቱ በፊት በእነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲሆኑ ያ ቀድሞውኑ ያውቁት የነበረ ነገር በመጣላቸው ጊዜ በእርሱ ካዱ:: እናም የአላህ እርግማን በካሐዲያን ላይ ይሁን፡፡
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከነሱም ጋር ያለውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የኾነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ (ከመምጣቱ) በፊት በነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲኾኑ ያወቁት ነገር በመጣላቸው ጊዜ በርሱ ካዱ፡፡ የአላህም ርግማን በከሓዲዎች ላይ ይኹን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70