caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Baqara፣ አንቀጽ 102

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 87 · 2:102

وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌ فَلَا تَكْفُرْ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ وَمَا هُم بِضَآرِّينَ بِهِۦ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَلَقَدْ عَلِمُوا۟ لَمَنِ ٱشْتَرَىٰهُ مَا لَهُۥ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنْ خَلَٰقٍ وَلَبِئْسَ مَا شَرَوْا۟ بِهِۦٓ أَنفُسَهُمْ لَوْ كَانُوا۟ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy102. (የአላህን መጽሐፍ አንቀበልም ያሉ አይሁዶች) ሰይጣናት በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ድግምት ተከተሉ:: ሱለይማን ጌታውን አልካደም::( ድግምተኛ አልነበረም::) ሰይጣናት ግን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲሆኑ በጌታቸው ካዱ:: በባቢሎን (በባቢል) በሁለቱ መላዕክት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደውን ተከተሉ:: (ሀሩትና ማሩት) ግን «እኛ ለእናንተ መፍፈተኛዎች ነንና በጌታህ አትካድ» እስከሚሉ ድረስ አንድንም አያስተምሩም ነበር:: ከእነርሱም በባልና በሚስቱ መካከል የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ:: እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንድንም በርሱ አይጎዱም:: (ድግምት የሚማሩ ሁሉ) የሚጎዳቸውንና ቅንጣት የማይጠቅማቸውን ትምህርት ይማራሉ:: የገዛው በመጨረሻይቱ አገር ምንም ዕድል የሌለው መሆኑን በእርግጥ ተገንዝበዋል:: ነፍሶቻቸውን የሸጡበት ዋጋ ምንኛ ከፋ:: የሚያውቁ በሆኑ ኑሮ (ይህን ተግባር ባልተገበሩት ነበር::)
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ (ድግምተኛ አልነበረም)፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር (ያስተምሩዋቸዋል)፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ፡፡ የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም እድል የሌለው መኾኑን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ ነፍሶቻቸውንም በርሱ የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በኾኑ ኖሮ (ባልሠሩት ነበር)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70