إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِى بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِّلْعَٰلَمِينَ
Amharic Translation - Africa Academy96. ለሰዎች (ማምለኪያ ይሆን ዘንድ በመሬት ላይ) በመጀመሪያ የተሰራው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲሆን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ቤት (ካዕባ) ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለሰዎች (የአላህ ማምለኪያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው፡፡