وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ أَفَإِي۟ن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ ٱنقَلَبْتُمْ عَلَىٰٓ أَعْقَٰبِكُمْ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ ٱللَّهَ شَيْـًٔا وَسَيَجْزِى ٱللَّهُ ٱلشَّٰكِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy144. (መልዕክተኛችን) ሙሐመድ ከበፊቱ ብዙ መልዕክተኞች እንዳለፉት የሆነ መልዕክተኛ እንጂ አይደለም:: ታዲያ እሱ ቢሞት ወይ ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደ ኋላው የሚቀለበስም አላህን ምንም አይጎዳም:: አላህ አመስጋኞቹን ተገቢዉን ይመነዳልና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደ ኋላው የሚገለበጥ ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህ አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡