ثُمَّ أَنزَلَ عَلَيْكُم مِّنۢ بَعْدِ ٱلْغَمِّ أَمَنَةً نُّعَاسًا يَغْشَىٰ طَآئِفَةً مِّنكُمْ وَطَآئِفَةٌ قَدْ أَهَمَّتْهُمْ أَنفُسُهُمْ يَظُنُّونَ بِٱللَّهِ غَيْرَ ٱلْحَقِّ ظَنَّ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ يَقُولُونَ هَل لَّنَا مِنَ ٱلْأَمْرِ مِن شَىْءٍ قُلْ إِنَّ ٱلْأَمْرَ كُلَّهُۥ لِلَّهِ يُخْفُونَ فِىٓ أَنفُسِهِم مَّا لَا يُبْدُونَ لَكَ يَقُولُونَ لَوْ كَانَ لَنَا مِنَ ٱلْأَمْرِ شَىْءٌ مَّا قُتِلْنَا هَٰهُنَا قُل لَّوْ كُنتُمْ فِى بُيُوتِكُمْ لَبَرَزَ ٱلَّذِينَ كُتِبَ عَلَيْهِمُ ٱلْقَتْلُ إِلَىٰ مَضَاجِعِهِمْ وَلِيَبْتَلِىَ ٱللَّهُ مَا فِى صُدُورِكُمْ وَلِيُمَحِّصَ مَا فِى قُلُوبِكُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
Amharic Translation - Africa Academy154. ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ:: ከፊሎችንም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው:: እውነት ያልሆነውን የመሀይምነትን መጠራጠር በአላህ ላይ ይጠራጠራሉ:: «በነገሩ ላይ ምንም የመወሰን መብት አለን? (የለንም።») ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመወሰን መብት ሁሉ የአላህ ብቻ ነው።» በላቸው:: ላንተ ግልጽ የማያደርጉትን በልቦቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ:: «የመወሰን መብት ቢኖረን ኖሮ በዚህ ቦታ ላይ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቤታችሁ ውስጥ በሆናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጸፈባቸው ወደየመውደቂያቸው በወጡ ነበር።» በላቸው:: አላህ ፍርዱን ሊፈጽምና በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ ይህንን ሰራ:: አላህ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር ሳይቀር አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከእናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ፡፡ ከፊሎቹም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው፡፡ እውነት ያልኾነውን የመሃይምነትን መጠራጠር በአላህ ይጠራጠራሉ፤ «ከነገሩ ለእኛ ምን አለልን? (ምንም የለንም)» ይላሉ፡፡ «ነገሩ ሁሉም ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ለአንተ የማይገልጹትን በነፍሶቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ፡፡ «ከነገሩ ለእኛ አንዳች በነበረን ኖሮ እዚህ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ፡፡ «በቤቶቻችሁ ውስጥ በኾናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጻፈባቸው ወደ መውደቂያቸው በወጡ ነበር» በላቸው፡፡ አላህ (ፍርዱን ሊፈጽምና) በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ (ይህን ሠራ)፡፡ አላህም በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡