فَتَقَبَّلَهَا رَبُّهَا بِقَبُولٍ حَسَنٍ وَأَنۢبَتَهَا نَبَاتًا حَسَنًا وَكَفَّلَهَا زَكَرِيَّا كُلَّمَا دَخَلَ عَلَيْهَا زَكَرِيَّا ٱلْمِحْرَابَ وَجَدَ عِندَهَا رِزْقًا قَالَ يَٰمَرْيَمُ أَنَّىٰ لَكِ هَٰذَا قَالَتْ هُوَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ يَرْزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ
Amharic Translation - Africa Academy37. ጌታዋም በመልካም አቀባበል ተቀበላት:: በመልካም አስተዳደግም አፋፋት:: ከዚያም ዘከርያ አሳደጋት:: ዘከርያም ወደ ምኩራቧ በሷ ላይ በገባ ቁጥርም እርሷ ዘንድ ሲሳይን አገኘ:: «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው የሚመጣልሽ?» አላት። «እርሱ የሚመጣልኝ ከአላህ ዘንድ ነው:: አላህ እኮ ለሚሻው ሁሉ ሲሳዩን ያለ ሂሳብ ይሰጣል።» አለችው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታዋም በደህና አቀባበል ተቀበላት፡፡ በመልካም አስተዳደግም አፋፋት፡፡ ዘከሪያም አሳደጋት፤ ዘከሪያ በርሷ ላይ በምኹራቧ በገባ ቁጥር እርስዋ ዘንድ ሲሳይን አገኘ፡፡ «መርየም ሆይ! ይህ ለአንቺ ከየት ነው» አላት፡፡ «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነው፡፡ አላህ ለሚሻው ሰው ሲሳዩን ያለ ድካም ይሰጣል» አለችው፡፡