caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 199

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:199

وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَمَن يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَٰشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ

Amharic Translation - Africa Academy199. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከል አላህን ፈሪዎችና በአላህ አናቅጽም ጥቂትን ዋጋ የማይለውጡ ሲሆኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው ቁርኣን በዚያም ወደ እነርሱ በተወረዱት ልዩ ልዩ መጽሐፍት የሚያምኑ ሰዎች አሉ:: እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ተገቢው ምንዳቸው አለላቸው አላህ ምርመራው ፈጣን ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው በዚያም ወደእነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አልሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70