إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ وَمَا ٱخْتَلَفَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ وَمَن يَكْفُرْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ
Amharic Translation - Africa Academy19. አላህ ዘንድ የተወደደው ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎች በመካከላቸው ባለው ምቀኝነት እውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም:: በአላህ አናቅጽ ለሚክድ ሁሉ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች በመካከላቸው ላለው ምቀኝነት ዕውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም፡፡ በአላህ አንቀጾች የሚክድ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡