وَلَا تُؤْمِنُوٓا۟ إِلَّا لِمَن تَبِعَ دِينَكُمْ قُلْ إِنَّ ٱلْهُدَىٰ هُدَى ٱللَّهِ أَن يُؤْتَىٰٓ أَحَدٌ مِّثْلَ مَآ أُوتِيتُمْ أَوْ يُحَآجُّوكُمْ عِندَ رَبِّكُمْ قُلْ إِنَّ ٱلْفَضْلَ بِيَدِ ٱللَّهِ يُؤْتِيهِ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ وَٰسِعٌ عَلِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy73. (አሉም) «ሃይማኖታችሁን ለተከተለ እንጂ አትመኑም።» (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ትክክለኛው መመሪያ የአላህ መመሪያ ብቻ ነው። እናንተ ያገኛችሁትን እድል እንዳያገኙ ወይም በእርሱ ከጌታችሁ ፊት እንዳይሞግቷችሁ በመፍራት ነውን?» በላቸው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ችሮታ በአላህ እጅ ብቻ ነው። ለሚፈልገውም ይሰጠዋል። አላህም ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ የተሰጣችሁትን ብጤ አንድም ሰው መሰጠቱን ወይም እጌታችሁ ዘንድ የሚከራከሩዋችሁ መኾንን ሃይማኖታችሁን ለተከተለ ሰው ቢኾን እንጂ አትመኑ (አትግለጹ አሉ)፡፡ «መምሪያው የአላህ መምሪያ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ «ችሮታ በአላህ እጅ ነው፡፡ ለሚሻው ይሰጠዋል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡