caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 118

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:118

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا۟ مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ ٱلْبَغْضَآءُ مِنْ أَفْوَٰهِهِمْ وَمَا تُخْفِى صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ ٱلْـَٔايَٰتِ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy118. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሚስጥረኛን (የልብ ወዳጅ) ከእናንተ ሌላ ከሆኑት አታድርጉ። የእናንተን ጉዳይ ከማበላሸት አይቦዝኑላችሁምና። ጉዳታችሁን ይወዳሉና (ይመኛሉ)። ለእናንተ ያላቸው ጥላቻ ከአፎቻቸው ላይ እንኳ ተገለጸ:: በልቦቻቸው የሚደብቁት ደግሞ ከዚህ ይበልጥ የከፋ ነው:: ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70