إِذْ تُصْعِدُونَ وَلَا تَلْوُۥنَ عَلَىٰٓ أَحَدٍ وَٱلرَّسُولُ يَدْعُوكُمْ فِىٓ أُخْرَىٰكُمْ فَأَثَٰبَكُمْ غَمًّۢا بِغَمٍّ لِّكَيْلَا تَحْزَنُوا۟ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمْ وَلَا مَآ أَصَٰبَكُمْ وَٱللَّهُ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy153. (የመልዕክተኛችን ሙሐመድ ባልደረቦች ሆይ!) መልዕክተኛው ከኋላችሁ ሁኖ እየጠራችሁ የማትዞሩ ሆናችሁ በርቀት በምትሸሹ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ባመለጣችሁ እድልና በደረሰባችሁም ነገር አለማዘንን ሊያስተምራችሁ በሀሳብ ላይ ሀሳብን አደረሰባችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውሰጠ አዋቂ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመልክተኛው ከኋላችሁ የሚጠራችሁ ሲኾን ርቃችሁ በምትሸሹና በአንድም ላይ የማትዞሩ በኾናችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ባመለጣችሁና በደረሰባችሁም ነገር እንድታዝኑ በሐሳብ ላይ ሐሳብን መነዳችሁ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡