ٱلَّذِينَ يَذْكُرُونَ ٱللَّهَ قِيَٰمًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِى خَلْقِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَٰطِلًا سُبْحَٰنَكَ فَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ
Amharic Translation - Africa Academy191. እነርሱም እነዚያ ቆመው ተቀምጠዉም በጎኖቻቸው ተጋድመዉም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑና (እንዲህም) የሚሉ ናቸው: «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከዉም ጥራት ይገባህ:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq(እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡