caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 78

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:78

وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُۥنَ أَلْسِنَتَهُم بِٱلْكِتَٰبِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمَا هُوَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy78. ከእነርሱም መካከል ከመጽሐፉ ያልሆነን ነገር ከመጽሐፉ አካል መሆኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙም አሉ:: እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልመጣ (ያልወረደ) ሲሆን «ከአላህ ዘንድ የመጣ (የወረደ) ነው።» ይላሉ። የሚያውቁ ሲሆኑ በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከእነሱም በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70