caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 112

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:112

ضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ ٱلذِّلَّةُ أَيْنَ مَا ثُقِفُوٓا۟ إِلَّا بِحَبْلٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَحَبْلٍ مِّنَ ٱلنَّاسِ وَبَآءُو بِغَضَبٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَضُرِبَتْ عَلَيْهِمُ ٱلْمَسْكَنَةُ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانُوا۟ يَكْفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقْتُلُونَ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَوا۟ وَّكَانُوا۟ يَعْتَدُونَ

Amharic Translation - Africa Academy112. በየተገኙበት ስፍራ ከአላህ በሆነ ቃልኪዳን ወይም ከሰዎች በሆነ ቃል ኪዳን የተጠበቁ ካልሆኑ በስተቀር በእነርሱ ላይ ውርደት ተጽፎባቸዋል። ከአላህ በሆነ ቁጣ ተመለሱ። ድህነትም በእነርሱ ላይ ተፅፎባቸዋል። ይህ የሆነውም በአላህ ተዐምራት (አናቅጽ) ይክዱ፤ ነቢያትንም ያላ አግባብ ይገድሉ ስለነበሩ ነው:: ይህም የሆነው በማመፃቸውና ወሰንን ይተላለፉ ስለነበሩ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበነርሱ ላይ ውርደት ተመታችባቸው የትም በተገኙበት ስፍራ ከአላህ በኾነ ቃል ኪዳን ከሰዎችም በኾነ ቃል ኪዳን (የተጠበቁ) ካልኾኑ በስተቀር ፡፡ ከአላህም በኾነ ቁጣ ተመለሱ፡፡ በእነርሱም ላይ ድኽነት ተመታችባቸው፡፡ ይኸ እነርሱ በአላህ ተዓምራት ይክዱ ስለ ነበሩና ነቢያትንም ያለ ሕግ ይገድሉ ስለነበሩ ነው፡፡ ይህ በማመጻቸውና ወሰንን ይተላለፉ ስለነበሩ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70