caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Nisaa النساء

176 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 92

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمُ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَٰحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَآءً وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ٱلَّذِى تَسَآءَلُونَ بِهِۦ وَٱلْأَرْحَامَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy1. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን፤ ከእርሷም መቀናጆዋን (ሀዋን) የፈጠረውንና ከሁለቱም ብዙ ወንዶችንና ብዙ ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ:: ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አላህን (ከሚያስቆጡ) ተግባራትና ዝምድናዎችን (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ:: አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاتُوا۟ ٱلْيَتَٰمَىٰٓ أَمْوَٰلَهُمْ وَلَا تَتَبَدَّلُوا۟ ٱلْخَبِيثَ بِٱلطَّيِّبِ وَلَا تَأْكُلُوٓا۟ أَمْوَٰلَهُمْ إِلَىٰٓ أَمْوَٰلِكُمْ إِنَّهُۥ كَانَ حُوبًا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy(እናንተ ኑዛዜ ተቀባዮች ሆይ! ) ለየቲሞች ገንዘቦቻቸውን ስጡ:: (ከመሀከሉም) መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ ገንዘቦቻችሁ (በመቀላቀል) አትብሉ:: እርሱ ትልቅ ኃጢአት ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا۟ فِى ٱلْيَتَٰمَىٰ فَٱنكِحُوا۟ مَا طَابَ لَكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ مَثْنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا۟ فَوَٰحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَلَّا تَعُولُوا۟

Amharic Translation - Africa Academy3. (እናንተ ሙስሊም ወንዶች ሆይ) በናንተ ስር ያሉት ሴት የቲሞችን በማግባታችሁ አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ከሴቶች መካከል ለእናንተ የመረጣችሁትን (ደስ ያሏችሁን) ሁለት ሁለት ሶስት ሶስትና አራት አራት አግቡ:: በሚስቶች መካከል አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ ግን አንዲትን ሴት ብቻ ወይም ንብረታችሁ የሆኑት ሴት ባሪያዎችን ብቻ (በሚስትነት) ያዙ:: ይህም (ሴትን ልጅ) እንዳትበድሉ በጣም የቀረበ ተግባር ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَءَاتُوا۟ ٱلنِّسَآءَ صَدُقَٰتِهِنَّ نِحْلَةً فَإِن طِبْنَ لَكُمْ عَن شَىْءٍ مِّنْهُ نَفْسًا فَكُلُوهُ هَنِيٓـًٔا مَّرِيٓـًٔا

Amharic Translation - Africa Academy4. ለሴቶች መህሮቻቸውን ደስተኞች ሆናችሁ ስጧቸው። ለእናንተ ከእርሱ የተወሰነን ነገር ራሳቸው ቢለግሱላችሁ ግን በእርካታና በምቾት ሆናችሁ ብሉት (ተጠቀሙበት)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُؤْتُوا۟ ٱلسُّفَهَآءَ أَمْوَٰلَكُمُ ٱلَّتِى جَعَلَ ٱللَّهُ لَكُمْ قِيَٰمًا وَٱرْزُقُوهُمْ فِيهَا وَٱكْسُوهُمْ وَقُولُوا۟ لَهُمْ قَوْلًا مَّعْرُوفًا

Amharic Translation - Africa Academy5. (ኃላፊዎች ሆይ!) ያን አላህ ለእናንተ መቋቋሚያ (መጠቃቀሚያ) ያደረገላችሁን ገንዘባችሁን (የያዛችሁላቸውን) ለቂሎች (ለአዕምሮ ደካሞች) አትስጧቸው:: ከእርሷም መግቧቸው:: ከእርሷ አልብሷቸዉም:: ለእነርሱም መልካምን ንግግር ተናገሯቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱبْتَلُوا۟ ٱلْيَتَٰمَىٰ حَتَّىٰٓ إِذَا بَلَغُوا۟ ٱلنِّكَاحَ فَإِنْ ءَانَسْتُم مِّنْهُمْ رُشْدًا فَٱدْفَعُوٓا۟ إِلَيْهِمْ أَمْوَٰلَهُمْ وَلَا تَأْكُلُوهَآ إِسْرَافًا وَبِدَارًا أَن يَكْبَرُوا۟ وَمَن كَانَ غَنِيًّا فَلْيَسْتَعْفِفْ وَمَن كَانَ فَقِيرًا فَلْيَأْكُلْ بِٱلْمَعْرُوفِ فَإِذَا دَفَعْتُمْ إِلَيْهِمْ أَمْوَٰلَهُمْ فَأَشْهِدُوا۟ عَلَيْهِمْ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ حَسِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy6. (ሙስሊሞች ሆይ!) የቲሞችን ለጋብቻ እስከደረሱ ድረስ ፈትኗቸው:: ከእነርሱም ብልህነትን ብታውቁ ገንዘቦቻቸውን ስጧቸው:: በማባከንና ማደጋቸውን በመሽቀዳደም ገንዘቦቻቸውን አትብሉባቸው:: (ከአሳዳጊዎቹ መካከል) ሀብታም የሆነ ሰው ከገንዘቦቻቸው (ቅንጣት ያህል እንኳን ከመቅረብ) ይከልከል:: ደሃ የሆነ ሰዉም ቢሆን ለድካሙ ብቻ በአግባቡ ይብላ:: ገንዘቦቻቸውን ወደ እነርሱ በሰጣችሁም ጊዜ በእነርሱ ላይ አስመስክሩ:: በተጠባባቂነትም አላህ በቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا تَرَكَ ٱلْوَٰلِدَانِ وَٱلْأَقْرَبُونَ وَلِلنِّسَآءِ نَصِيبٌ مِّمَّا تَرَكَ ٱلْوَٰلِدَانِ وَٱلْأَقْرَبُونَ مِمَّا قَلَّ مِنْهُ أَوْ كَثُرَ نَصِيبًا مَّفْرُوضًا

Amharic Translation - Africa Academy7. ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ሲሞቱ ከተውት (ጥሪት ገንዘብ የውርስ) ድርሻ አላቸው:: ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ከእርሱ ይነስም ይብዛም (የውርስ) ድርሻ አላቸው:: ለሁሉም የተወሰነ ድርሻ ተደንግጓል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا حَضَرَ ٱلْقِسْمَةَ أُو۟لُوا۟ ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينُ فَٱرْزُقُوهُم مِّنْهُ وَقُولُوا۟ لَهُمْ قَوْلًا مَّعْرُوفًا

Amharic Translation - Africa Academy8. የውርስ ክፍፍልን (ወራሽ ያልሆኑ) የዝምድና ባለቤቶች፤ የቲሞችና ሚስኪኖች በተገኙበት ጊዜ ከእርሱ ለግሱላቸው:: መልካምንም ንግግር ተናገሯቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلْيَخْشَ ٱلَّذِينَ لَوْ تَرَكُوا۟ مِنْ خَلْفِهِمْ ذُرِّيَّةً ضِعَٰفًا خَافُوا۟ عَلَيْهِمْ فَلْيَتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلْيَقُولُوا۟ قَوْلًا سَدِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy9. እነዚያ ከኋላቸው ደካማ ዝርያዎችን ቢተው ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ይደርስባቸው ይሆን ብለው የሚሰጉ ሰዎች ሁሉ (በየቲሞችም ላይ) ይህንኑ ይፍሩ:: አላህንም ይፍሩ:: ትክክለኛንም ቃል ይናገሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَأْكُلُونَ أَمْوَٰلَ ٱلْيَتَٰمَىٰ ظُلْمًا إِنَّمَا يَأْكُلُونَ فِى بُطُونِهِمْ نَارًا وَسَيَصْلَوْنَ سَعِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ የየቲሞችን ገንዘቦች በግፍ የሚበሉ ሁሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳትን ብቻ ነው:: የገሀንም እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُوصِيكُمُ ٱللَّهُ فِىٓ أَوْلَٰدِكُمْ لِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ ٱلْأُنثَيَيْنِ فَإِن كُنَّ نِسَآءً فَوْقَ ٱثْنَتَيْنِ فَلَهُنَّ ثُلُثَا مَا تَرَكَ وَإِن كَانَتْ وَٰحِدَةً فَلَهَا ٱلنِّصْفُ وَلِأَبَوَيْهِ لِكُلِّ وَٰحِدٍ مِّنْهُمَا ٱلسُّدُسُ مِمَّا تَرَكَ إِن كَانَ لَهُۥ وَلَدٌ فَإِن لَّمْ يَكُن لَّهُۥ وَلَدٌ وَوَرِثَهُۥٓ أَبَوَاهُ فَلِأُمِّهِ ٱلثُّلُثُ فَإِن كَانَ لَهُۥٓ إِخْوَةٌ فَلِأُمِّهِ ٱلسُّدُسُ مِنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِى بِهَآ أَوْ دَيْنٍ ءَابَآؤُكُمْ وَأَبْنَآؤُكُمْ لَا تَدْرُونَ أَيُّهُمْ أَقْرَبُ لَكُمْ نَفْعًا فَرِيضَةً مِّنَ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy11. (ሰዎች ሆይ) አላህ በልጆቻችሁ ውርስ (በሚከተለው መልኩ) ያዛችኋል:: ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው:: (ሁለት ወይም) ከሁለት በላይ የሆኑ ሴቶች ልጆች ብቻ ወራሽ ቢሆኑ ለእነርሱ (ሟቹ) ከተወው (ሀብት) ከሶስት ሁለት እጁ ያገኛሉ (አላቸው):: አንዲት ሴት ወራሽ ብትሆን ደግሞ ለእርሷ የሀብቱ ግማሽ አላት:: ለሟቹ ልጅ ካለው ለአባቱና ለእናቱ ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው:: ለእርሱ ልጅ ባይኖረውና ወላጆቹ ብቻ ቢወርሱት ለእናቱ ሲሶው አላት:: ለእርሱም ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩት ለእናቱ ከስድስት አንድ አላት:: (ይህም ውርስ) የሚከፋፈለው ከተናዘዘው ኑዛዜ ወይም ከእዳው ክፍያ በኋላ ነው:: አባቶቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ በመጥቀም ማንኛቸው ይበልጥ ቅርብ እንደሆኑ አታውቁም:: ይህም ከአላህ የተደነገገ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَكُمْ نِصْفُ مَا تَرَكَ أَزْوَٰجُكُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّهُنَّ وَلَدٌ فَإِن كَانَ لَهُنَّ وَلَدٌ فَلَكُمُ ٱلرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْنَ مِنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصِينَ بِهَآ أَوْ دَيْنٍ وَلَهُنَّ ٱلرُّبُعُ مِمَّا تَرَكْتُمْ إِن لَّمْ يَكُن لَّكُمْ وَلَدٌ فَإِن كَانَ لَكُمْ وَلَدٌ فَلَهُنَّ ٱلثُّمُنُ مِمَّا تَرَكْتُم مِّنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ تُوصُونَ بِهَآ أَوْ دَيْنٍ وَإِن كَانَ رَجُلٌ يُورَثُ كَلَٰلَةً أَوِ ٱمْرَأَةٌ وَلَهُۥٓ أَخٌ أَوْ أُخْتٌ فَلِكُلِّ وَٰحِدٍ مِّنْهُمَا ٱلسُّدُسُ فَإِن كَانُوٓا۟ أَكْثَرَ مِن ذَٰلِكَ فَهُمْ شُرَكَآءُ فِى ٱلثُّلُثِ مِنۢ بَعْدِ وَصِيَّةٍ يُوصَىٰ بِهَآ أَوْ دَيْنٍ غَيْرَ مُضَآرٍّ وَصِيَّةً مِّنَ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy12. ለእናንተም ሚስቶቻችሁ ከተውት ንብረት ለእነርሱ ልጅ ካልኖራቸው ግማሹ አላችሁ:: ለእነርሱም ልጅ ቢኖራቸው ከተውት ሀብት ከአራት አንድ አላችሁ :: (ይህም) በእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ለእናንተም ልጅ ከሌላችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) አንድ አራተኛ አላቸው። ለእናንተም ልጅ ባይኖራችሁ ከተዋችሁት ንብረት ለእነርሱ (ለሚስቶቻችሁ) ከስምንት አንድ አላቸው:: (ይህም) ከምትናዘዙበት ኑዛዜ ወይም ከእዳ ክፍያ በኋላ ነው:: ወላጆችም ልጅም የሌለውና የጎን ወራሾች የሚወርሱት ወንድ ወይም ሴት ቢገኝ ለእርሱም (ለሟቹ) ከእናቱ በኩል ብቻ የሆኑ ወንድም ወይም እህት ቢኖሩት ከሁለቱ ለእያንደንዳቸው ከስድስት አንድ አላቸው:: ከአንድ የበዙ ቢሆኑ ደግሞ በሲሶው ላይ ተጋሪዎች ናቸው:: ይህም ወራሾቹን የማይጎዳ ሆኖ ከእርሷ ከሚናዘዙባት ኑዛዜ ወይም ከእዳ በኋላ ነው:: ከአላህም የሆነን ኑዛዜ ያዛችኋል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ቻይ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ يُدْخِلْهُ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy13. እነዚህ የአላህ ውሳኔዎች ናቸው:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዙ ሰዎች ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል። ይህም ትልቅ እድል ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَعْصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَتَعَدَّ حُدُودَهُۥ يُدْخِلْهُ نَارًا خَٰلِدًا فِيهَا وَلَهُۥ عَذَابٌ مُّهِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy14. በአላህና በመልዕክተኛው ላይ የሚያምጽ ወሰኖችንም የሚተላለፍ ሁሉ በውስጧ ዘውታሪ ሲሆን ወደ ገሀነም እሳት ያስገባዋል:: ለእርሱም አዋራጅ ቅጣት አለበት።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّٰتِى يَأْتِينَ ٱلْفَٰحِشَةَ مِن نِّسَآئِكُمْ فَٱسْتَشْهِدُوا۟ عَلَيْهِنَّ أَرْبَعَةً مِّنكُمْ فَإِن شَهِدُوا۟ فَأَمْسِكُوهُنَّ فِى ٱلْبُيُوتِ حَتَّىٰ يَتَوَفَّىٰهُنَّ ٱلْمَوْتُ أَوْ يَجْعَلَ ٱللَّهُ لَهُنَّ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy15. እነዚያ ከሴቶቻችሁ መካከል ዝሙትን የሚሰሩ በእነርሱ ላይ ከናንተ የሆነን አራት ታማኝ ወንዶችን አስመስክሩባቸው:: ከመሰከሩባቸዉም ሞት እስከሚደርስባቸው ወይም አላህ ለእነርሱ ሌላ መንገድን እስከሚያደርግ ድረስ በቤቶች ውስጥ ያዟቸው(እሰሯቸው::)

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذَانِ يَأْتِيَٰنِهَا مِنكُمْ فَـَٔاذُوهُمَا فَإِن تَابَا وَأَصْلَحَا فَأَعْرِضُوا۟ عَنْهُمَآ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ تَوَّابًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy16. እነዚያ ከእናንተ ውስጥ ዝሙትን የሚሰሩትን አሰቃዩዋቸው (በሚገባ ቅጧቸው):: ቢጸጸቱና ስራቸውን ቢያሳምሩ ግን እነርሱን ተዋቸው (አታሰቃዩዋቸው።) አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّمَا ٱلتَّوْبَةُ عَلَى ٱللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ ٱلسُّوٓءَ بِجَهَٰلَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٍ فَأُو۟لَٰٓئِكَ يَتُوبُ ٱللَّهُ عَلَيْهِمْ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy17. ጸጸትን መቀበል ከአላህ በኩል ለእነዚያ ኃጢአትን በስህተት ለሚሰሩና ከዚያም ወዲያውኑ ለሚጸጸቱ ነው:: እነዚያንማ አላህ ከእነርሱ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና፣

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَيْسَتِ ٱلتَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ حَتَّىٰٓ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ ٱلْمَوْتُ قَالَ إِنِّى تُبْتُ ٱلْـَٰٔنَ وَلَا ٱلَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ أُو۟لَٰٓئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy18. ጸጸትን መቀበል ለእነዚያ ኃጢአቶችን ለሚሰሩና ልክ ሞት በመጣባቸው ጊዜ «አሁን ተጸጸትኩ።» ለሚሉና ለእነዚያም ከሓዲያን ሆነው ለሚሞቱ አይደለም:: ለእነርሱማ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا۟ ٱلنِّسَآءَ كَرْهًا وَلَا تَعْضُلُوهُنَّ لِتَذْهَبُوا۟ بِبَعْضِ مَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ إِلَّآ أَن يَأْتِينَ بِفَٰحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ فَإِن كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًٔا وَيَجْعَلَ ٱللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy19. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ሆናችሁ ልትወርሱና ግልጽ የሆነ መጥፎ ስራ ካልሰሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱባቸውና ልታጉላሏዋቸው አይፈቀድላችሁም:: በመልካም ተኗኗሯቸው:: ብትጠሏቸዉም እንኳን ታገሱ:: አንድ ነገር ብትጠሉትም አላህ በእርሱ ዉስጥ ብዙ ደግ ነገሮችን ሊያደርግላችሁ ይችላልና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنْ أَرَدتُّمُ ٱسْتِبْدَالَ زَوْجٍ مَّكَانَ زَوْجٍ وَءَاتَيْتُمْ إِحْدَىٰهُنَّ قِنطَارًا فَلَا تَأْخُذُوا۟ مِنْهُ شَيْـًٔا أَتَأْخُذُونَهُۥ بُهْتَٰنًا وَإِثْمًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy20. (ባሎች ሆይ!) በሚስት ቦታ ሌላ ሚስትን ለመለወጥ ብትፈልጉ (ለምትፈታው ሴት ቀደም ሲል) ብዙን ገንዘብ የሰጣችኋት እንደሆነ ከእርሷ ምንንም አትውሰዱባት:: በመበደልና ግልጽ በሆነ ኃጢአት ትወስዱታላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَيْفَ تَأْخُذُونَهُۥ وَقَدْ أَفْضَىٰ بَعْضُكُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ وَأَخَذْنَ مِنكُم مِّيثَٰقًا غَلِيظًا

Amharic Translation - Africa Academy21. ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ የደረሰ ሲሆንና ከናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ቃል ኪዳንን የያዙባችሁ ሲሆኑ እንዴት ትወስዱታላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَنكِحُوا۟ مَا نَكَحَ ءَابَآؤُكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةً وَمَقْتًا وَسَآءَ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy22. (ወንዶች ሆይ!) ከሴቶች መካከል አባቶቻችሁ ያገቧቸውን አታግቡ። ያለፈው ሲቀር። እርሱ መጥፎና የተጠላ ስራ ነውና። መንገድነቱም ከፋ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَٰتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَٰتُكُمْ وَعَمَّٰتُكُمْ وَخَٰلَٰتُكُمْ وَبَنَاتُ ٱلْأَخِ وَبَنَاتُ ٱلْأُخْتِ وَأُمَّهَٰتُكُمُ ٱلَّٰتِىٓ أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَٰتُكُم مِّنَ ٱلرَّضَٰعَةِ وَأُمَّهَٰتُ نِسَآئِكُمْ وَرَبَٰٓئِبُكُمُ ٱلَّٰتِى فِى حُجُورِكُم مِّن نِّسَآئِكُمُ ٱلَّٰتِى دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا۟ دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَٰٓئِلُ أَبْنَآئِكُمُ ٱلَّذِينَ مِنْ أَصْلَٰبِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا۟ بَيْنَ ٱلْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy23. (ወንዶች ሆይ!) እናቶቻችሁ፤ ሴት ልጆቻችሁ፤ እህቶቻችሁ፤ አክስቶቻችሁ (የአባቶቻችሁ እህቶች)፣ አክስቶቻችሁ (የእናቶቻችሁ እህቶች)፤ የወንድም ሴት ልጆች፤ የእህት ሴት ልጆች፤ እነዚያም ያጠቧችሁ የጡት እናቶቻችሁ፤ የጡት እህቶቻችሁ፤ የሚስቶቻችሁ እናቶች፤ እነዚያም ከጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ ግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸማችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴት ልጆች ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ:: ግብረ ስጋ ግንኙነት ያልፈጸማችሁባቸው የሚስቶቻችሁ ሴት ልጆቻቸውን ብታገቡ ግን በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የሆኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም ሁለት እህትማማቾችን በአንድ መሰብሰብም እንደዚሁ እርም ነው:: ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር:: እርሱንስ ተምራችኋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلنِّسَآءِ إِلَّا مَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ كِتَٰبَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَأُحِلَّ لَكُم مَّا وَرَآءَ ذَٰلِكُمْ أَن تَبْتَغُوا۟ بِأَمْوَٰلِكُم مُّحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ فَمَا ٱسْتَمْتَعْتُم بِهِۦ مِنْهُنَّ فَـَٔاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ فَرِيضَةً وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا تَرَٰضَيْتُم بِهِۦ مِنۢ بَعْدِ ٱلْفَرِيضَةِ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy24. ባል ያገቡ ሴቶችም በጦርነት እጆቻችሁ በምርኮ የያዟቸው ሲቀሩ (በእናንተ ላይ እርም ናቸው):: ይህን ህግ አላህ በእናንተ ላይ ደነገገ:: ከነዚህ ከተከለከሉት ሌላ ጥብቆች ሆናችሁና ዝሙተኞች ሳትሆኑ በገንዘባችሁ ጋብቻን ልትፈለጉ ለእናንተ ተፈቀደ:: እናም ከእነርሱም መገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች መህሮቻቸውን ልትሰጧቸው ግዴታ ነው:: ከመወሰን በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ مِنكُمْ طَوْلًا أَن يَنكِحَ ٱلْمُحْصَنَٰتِ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ فَمِن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُم مِّن فَتَيَٰتِكُمُ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَٰنِكُم بَعْضُكُم مِّنۢ بَعْضٍ فَٱنكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَءَاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ مُحْصَنَٰتٍ غَيْرَ مُسَٰفِحَٰتٍ وَلَا مُتَّخِذَٰتِ أَخْدَانٍ فَإِذَآ أُحْصِنَّ فَإِنْ أَتَيْنَ بِفَٰحِشَةٍ فَعَلَيْهِنَّ نِصْفُ مَا عَلَى ٱلْمُحْصَنَٰتِ مِنَ ٱلْعَذَابِ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَشِىَ ٱلْعَنَتَ مِنكُمْ وَأَن تَصْبِرُوا۟ خَيْرٌ لَّكُمْ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy25. (ወንዶች ሆይ!) ከናንተ መካከል ጥብቆች ምዕመናትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምዕመናት መካከል ወጣቶቻችሁን አገልጋዬች የመረጠውን ያግባ:: አላህ የውስጥ እምነታችሁን ምንነት አዋቂ ነውና:: ከፊላችሁ ከከፊሉ የተራባ ነው:: ባሮችንም ቢሆን እንደዚሁ በአሳዳሪዎቻቸው ፈቃድ ብቻ አግቧቸው:: መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው:: ጥብቆች ሆነው ዝሙተኛ ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጅንም ያልያዙ እንደሆኑ አግቧቸው:: በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ስራ ቢሰሩ በእነርሱ ላይ የተደነገገው ቅጣት በነፃዎቹ ላይ ከተደነገገው ቅጣት ግማሹ ቅጣት አለባቸው:: ያ ከናንተ መካከል ዝሙትን ለፈራ ብቻ ነው:: መታገሳችሁ የተሻለ ነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُبَيِّنَ لَكُمْ وَيَهْدِيَكُمْ سُنَنَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ وَيَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy26. (አማኞች ሆይ!) አላህ የሃይማኖታችሁን ህግጋት ሊያብራራላችሁ፤ ከናንተ በፊትም የነበሩትን ነብያት ፈለጎች ሊመራችሁ፤ በእናንተም ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يَتُوبَ عَلَيْكُمْ وَيُرِيدُ ٱلَّذِينَ يَتَّبِعُونَ ٱلشَّهَوَٰتِ أَن تَمِيلُوا۟ مَيْلًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy27. አላህ በእናንተ ላይ ጸጸትን ሊቀበል ይሻል:: እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚከተሉ ግን ከእውነት ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُخَفِّفَ عَنكُمْ وَخُلِقَ ٱلْإِنسَٰنُ ضَعِيفًا

Amharic Translation - Africa Academy28. አላህ ከናንተ ሊያቃልልላችሁ ይሻል። ሰው ደካማ ሆኖ የተፈጠረ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَأْكُلُوٓا۟ أَمْوَٰلَكُم بَيْنَكُم بِٱلْبَٰطِلِ إِلَّآ أَن تَكُونَ تِجَٰرَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ وَلَا تَقْتُلُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy29. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ:: በእናንተ መካከል በመስማማት የሆነችውን ንግድ ካልሆነች በስተቀር (እሷን ግን ብሉ) :: ነፍሶቻችሁን በራሳችሁ አትግደሉ። አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَٰنًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy30. ወሰን በማለፍ እና በመበደል ይህን የሰራ ሁሉ እሳት እናስገባዋለን:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تَجْتَنِبُوا۟ كَبَآئِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًا كَرِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy31. ትክክለኛ አማኞች ሆይ! ከተከለከላችሁት ወንጀሎች መካክል ታላላቆችን ብትርቁ ትናንሽ ኃጢአቶቻችሁን እናብስላችኋለን:: የተከበረውንም መግቢያ (ገነት) እናስገባችኋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَتَمَنَّوْا۟ مَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بِهِۦ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا ٱكْتَسَبُوا۟ وَلِلنِّسَآءِ نَصِيبٌ مِّمَّا ٱكْتَسَبْنَ وَسْـَٔلُوا۟ ٱللَّهَ مِن فَضْلِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy32. አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ:: ለወንዶችም ከሰሩት ስራ እድል አለላቸው:: ለሴቶችም ከሰሩት ስራ እንዲሁ እድል አለላቸው:: አላህን ከችሮታው ለምኑት:: አላህ በሁሉ ነገር አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِكُلٍّ جَعَلْنَا مَوَٰلِىَ مِمَّا تَرَكَ ٱلْوَٰلِدَانِ وَٱلْأَقْرَبُونَ وَٱلَّذِينَ عَقَدَتْ أَيْمَٰنُكُمْ فَـَٔاتُوهُمْ نَصِيبَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy33. ለሁላችሁም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ሀብት ወራሾችን አድርገናል:: እነዚያንም (ለመረዳዳትና ለመዋረስ) በመሐላዎቻችሁ የተዋዋላችኋቸውን (ከስድስት አንድ) ድርሻቸውን ስጧቸው:: አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ (መስካሪ) ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلرِّجَالُ قَوَّٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَآءِ بِمَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَآ أَنفَقُوا۟ مِنْ أَمْوَٰلِهِمْ فَٱلصَّٰلِحَٰتُ قَٰنِتَٰتٌ حَٰفِظَٰتٌ لِّلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ ٱللَّهُ وَٱلَّٰتِى تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَٱهْجُرُوهُنَّ فِى ٱلْمَضَاجِعِ وَٱضْرِبُوهُنَّ فَإِنْ أَطَعْنَكُمْ فَلَا تَبْغُوا۟ عَلَيْهِنَّ سَبِيلًا إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيًّا كَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy34. ወንዶች ለሴቶች ቋሚና የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው:: አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ምክኒያት ነው:: መልካሞቹ ሴቶች ማለት ለባሎቻቸው ታዛዦች፤ አላህ ባስጠበቀው ነገር ከባሎቻቸው ሩቅ የሆነውን ጠባቂዎች ናቸው:: እነዚያን ማመፃቸውን የምትፈሩትን ሴቶች መጀመሪያ ገስጿቸው:: ከዚያም በመኝታቸው ተለዩዋቸው:: ከዚያም (በአካሎቻቸው ላይ ሳካ ሳታደርሱ) ምቷቸው:: ከታዘዟችሁ ለመጨቆን ስትሉ በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ:: አላህ የሁሉም በላይና ታላቅ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنْ خِفْتُمْ شِقَاقَ بَيْنِهِمَا فَٱبْعَثُوا۟ حَكَمًا مِّنْ أَهْلِهِۦ وَحَكَمًا مِّنْ أَهْلِهَآ إِن يُرِيدَآ إِصْلَٰحًا يُوَفِّقِ ٱللَّهُ بَيْنَهُمَآ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy35. በመካከላቸውም ጭቅጭቅ መኖሩን ብትፈሩ (ብታውቁ) ከቤተሰቡና ከቤተሰቦቿ የተውጣጡ የቤተ ዘመድ ጉባኤ አዋቅሩ:: ሁለቱም እርቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማቸዋል:: አላህ ግልጽንም ሆነ ውስጥንም አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا۟ بِهِۦ شَيْـًٔا وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًا وَبِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱلْجَارِ ذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْجَارِ ٱلْجُنُبِ وَٱلصَّاحِبِ بِٱلْجَنۢبِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَٰنُكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

Amharic Translation - Africa Academy36. አላህን ተገዙ:: በእርሱ ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች፣ ለቅርብ ዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለቅርብ ጎረቤት፣ ለሩቅ ጎረቤት፣ ለጎን ባልደረባ፣ ለመንገደኛ፣ እጆቻችሁ ንብረት ላደረጓቸው ባሮች መልካምን ስሩ። አላህ ኩራተኞችንና ጉረኞችን አይወድምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَبْخَلُونَ وَيَأْمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلْبُخْلِ وَيَكْتُمُونَ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَٰفِرِينَ عَذَابًا مُّهِينًا

Amharic Translation - Africa Academy37. እነዚያ የሚሰስቱ ንፉጎችና ሰዎችንም በመሰሰት (በንፍግና) የሚያዝዙ አላህ ከችሮታው የሰጣቸውን ጸጋ የሚደብቁ ብርቱን ቅጣት ይቀጣቸዋል። ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمْ رِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَلَا بِٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَمَن يَكُنِ ٱلشَّيْطَٰنُ لَهُۥ قَرِينًا فَسَآءَ قَرِينًا

Amharic Translation - Africa Academy38. እነዚያ ለሰዎች ይዩልን ሲሉ ገንዘቦቻቸውን የሚሰጡ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑ ይቀጣሉ:: ሰይጣንም የእሱ ጓደኛው የሆነለት ሁሉ ጓደኛነቱ ከፋ!

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَاذَا عَلَيْهِمْ لَوْ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَأَنفَقُوا۟ مِمَّا رَزَقَهُمُ ٱللَّهُ وَكَانَ ٱللَّهُ بِهِمْ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy39. በአላህና በመጨረሻው ቀን ባመኑና አላህ ከሰጣቸዉም ሲሳይ በለገሱ ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ጉዳት ነበረ? አላህ በእነርሱ ሁኔታ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَظْلِمُ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ وَإِن تَكُ حَسَنَةً يُضَٰعِفْهَا وَيُؤْتِ مِن لَّدُنْهُ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy40. አላህ የብናኝን ክብደት ያህል እንኳን አይበድልም:: መልካም ስራ ብትሆንም ይደራርባታል:: ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍۭ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦች ሁሉ መስካሪን ባመጣንና አንተንም በእነዚህ (ባንተ ህዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲያን ሁኔታ እንዴት ይሆን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَوْمَئِذٍ يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَعَصَوُا۟ ٱلرَّسُولَ لَوْ تُسَوَّىٰ بِهِمُ ٱلْأَرْضُ وَلَا يَكْتُمُونَ ٱللَّهَ حَدِيثًا

Amharic Translation - Africa Academy42. በዚያ ቀን እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችና መልዕክተኛውን ያልታዘዙት ምድር በእነርሱ ላይ ብትደፋባቸው ይመኛሉ:: ከአላህም ወሬን አይደብቁም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقْرَبُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنتُمْ سُكَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَعْلَمُوا۟ مَا تَقُولُونَ وَلَا جُنُبًا إِلَّا عَابِرِى سَبِيلٍ حَتَّىٰ تَغْتَسِلُوا۟ وَإِن كُنتُم مَّرْضَىٰٓ أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوْ جَآءَ أَحَدٌ مِّنكُم مِّنَ ٱلْغَآئِطِ أَوْ لَٰمَسْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَلَمْ تَجِدُوا۟ مَآءً فَتَيَمَّمُوا۟ صَعِيدًا طَيِّبًا فَٱمْسَحُوا۟ بِوُجُوهِكُمْ وَأَيْدِيكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّا غَفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy43. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የምትሉትን ነገር ለይታችሁ አስከምታውቁ ድረስ የሰከራችሁ ሆናችሁ ወደ ሶላት አትቅረቡ:: ጀናባ ስትሆኑም መንገድን አላፊዎች ካልሆናችሁ በስተቀር ሙሉ አካላታችሁን እስከምትታጥቡ ድረስ መስጊድን አትቅረቡ:: በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዱ ከአይነ ምድር ቢጸዳዳ ወይም ከሴቶች ጋር ብትነካኩና ( የግብረስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ ንጹህ የሆነን የምድር ገጽ (አፈርን) አብሱ:: ከዚያ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን በእርሱ አብሱ:: አላህ ይቅር ባይና መሀሪ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ نَصِيبًا مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ يَشْتَرُونَ ٱلضَّلَٰلَةَ وَيُرِيدُونَ أَن تَضِلُّوا۟ ٱلسَّبِيلَ

Amharic Translation - Africa Academy44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ የእውቀት ድርሻን ወደ ተሰጡት ክፍሎች አላየህም? ጥመትን በቅንነት ይገዛሉ:: መንገድንም እንድትሳሳቱ ይፈልጋሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱللَّهُ أَعْلَمُ بِأَعْدَآئِكُمْ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَلِيًّا وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy45. (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) አላህ ጠላቶቻችሁን ከናንተ በበለጠ አዋቂ ነው:: ጠባቂነትም በአላህ በቃ:: ረዳትነትም በአላህ በቃ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَيَقُولُونَ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَٱسْمَعْ غَيْرَ مُسْمَعٍ وَرَٰعِنَا لَيًّۢا بِأَلْسِنَتِهِمْ وَطَعْنًا فِى ٱلدِّينِ وَلَوْ أَنَّهُمْ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَٱسْمَعْ وَٱنظُرْنَا لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ وَأَقْوَمَ وَلَٰكِن لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy46. ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አሉ። «ንግግርክን ሰማንና ትእዛዝክን አመጽን፤ የማትሰማም ስትሆን እስቲ ስማ።» ይላሉ:: በምላሶቻቸዉም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ በማሰብ "ራዒና" ይላሉ:: እነርሱም «ሰማንና ታዘዝን፤ ስማን ተመልከተንም።» ባሉ ኖሮ ለእነርሱም መልካምና ትክክለኛ በሆነ ነበር:: ግን በክህደታቸው ምክንያት አላህ ረገማቸው:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች እንጂ አያምኑም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ ءَامِنُوا۟ بِمَا نَزَّلْنَا مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَكُم مِّن قَبْلِ أَن نَّطْمِسَ وُجُوهًا فَنَرُدَّهَا عَلَىٰٓ أَدْبَارِهَآ أَوْ نَلْعَنَهُمْ كَمَا لَعَنَّآ أَصْحَٰبَ ٱلسَّبْتِ وَكَانَ أَمْرُ ٱللَّهِ مَفْعُولًا

Amharic Translation - Africa Academy47. እናንተ መጽሐፉ የተሰጣችሁ ሰዎች ሆይ! ፊቶችን ሳናዞርና በጀርባዎች ላይ ሳንመልሳቸው ወይም የሠንበትን ባለቤቶች እንደረገምን ሳንረግማችሁ በፊት ከናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ሆኖ በአወረድነው ቁርኣን እመኑ:: የአላህም ትዕዛዝ ተፈፃሚ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِۦ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُ وَمَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱفْتَرَىٰٓ إِثْمًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy48. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከዚህ በታች (ውጭ) ያለውን ኃጢአት ግን ለሚሻው ሁሉ ይምራል:: በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يُزَكُّونَ أَنفُسَهُم بَلِ ٱللَّهُ يُزَكِّى مَن يَشَآءُ وَلَا يُظْلَمُونَ فَتِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy49. ወደ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ወደ ሚያጠሩት (ሚያወድሱት) አላየህምን? ይልቁንም አላህ ነው የሚፈልገውን የሚያጠራው። በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለችን ክር መሳይ ያህልም ቢሆን አይበደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱنظُرْ كَيْفَ يَفْتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ وَكَفَىٰ بِهِۦٓ إِثْمًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ውሸትን እንዴት እንደሚቀጥፉ ተመልከት። ግልጽ ወንጀል በርሱ በቃ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ نَصِيبًا مِّنَ ٱلْكِتَٰبِ يُؤْمِنُونَ بِٱلْجِبْتِ وَٱلطَّٰغُوتِ وَيَقُولُونَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا۟ هَٰٓؤُلَآءِ أَهْدَىٰ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ድርሻን ወደ ተሰጡት አላየህምን? በድግምትና በጣዖት ያምናሉ። ለእነዚያ በአላህ ለካዱትም እነርሱ በሃይማኖት ከእነዚያ በሙሐመድ ካመኑት ይበልጥ ቀና እንደሆኑ ይናገራሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ وَمَن يَلْعَنِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው:: አላህ የረገመውን ደግሞ ለርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝለትም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ لَهُمْ نَصِيبٌ مِّنَ ٱلْمُلْكِ فَإِذًا لَّا يُؤْتُونَ ٱلنَّاسَ نَقِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy53. በእውነቱ ለእነርሱ ከንግስናው ፈንታ አላቸውን? ያን ጊዜማ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ ያለችውን ነጥብ ያህል እንኳን አይሰጡም ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَمْ يَحْسُدُونَ ٱلنَّاسَ عَلَىٰ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦ فَقَدْ ءَاتَيْنَآ ءَالَ إِبْرَٰهِيمَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَءَاتَيْنَٰهُم مُّلْكًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy54. ይልቁንም ለሰዎች አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን? ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን:: ታላቅንም ንግስናን ሰጠናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمِنْهُم مَّنْ ءَامَنَ بِهِۦ وَمِنْهُم مَّن صَدَّ عَنْهُ وَكَفَىٰ بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy55. ከነሱም (ከአይሁድ) መካከል በነብዩ ሙሐመድ ያመነ አለ:: ከእነርሱም ከዚህ እምነት ያፈገፈገ አለ። አቃጣይነት በገሀነም በቃ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًا كُلَّمَا نَضِجَتْ جُلُودُهُم بَدَّلْنَٰهُمْ جُلُودًا غَيْرَهَا لِيَذُوقُوا۟ ٱلْعَذَابَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy56. እነዚያን በተዐምራታችን የካዱትን ሁሉ በእርግጥ እሳትን እናስገባቸዋለን:: ስቃይን እንዲቀምሱም ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا لَّهُمْ فِيهَآ أَزْوَٰجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَنُدْخِلُهُمْ ظِلًّا ظَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy57. እነዚያ በአላህ አንድነት ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናስገባቸዋለን:: ለእነርሱ በውስጧ ንጹህ ሚስቶችም አሏቸው:: የምታስጠልልን ጥላም እናስገባቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا۟ ٱلْأَمَٰنَٰتِ إِلَىٰٓ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ ٱلنَّاسِ أَن تَحْكُمُوا۟ بِٱلْعَدْلِ إِنَّ ٱللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِۦٓ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ سَمِيعًۢا بَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy58. አላህ አደራዎችን ወደ የባለቤቶቻቸው እንድታደርሱና በሰዎች መካከል በፈረዳችሁ ጊዜም በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል:: አላህ በእርሱ የሚገስፃችሁ ነገር ምን ያምር ነው! አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَأُو۟لِى ٱلْأَمْرِ مِنكُمْ فَإِن تَنَٰزَعْتُمْ فِى شَىْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy59. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ:: መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يَزْعُمُونَ أَنَّهُمْ ءَامَنُوا۟ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوٓا۟ إِلَى ٱلطَّٰغُوتِ وَقَدْ أُمِرُوٓا۟ أَن يَكْفُرُوا۟ بِهِۦ وَيُرِيدُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَن يُضِلَّهُمْ ضَلَٰلًۢا بَعِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ «ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊትም በተወረደው አምነናል።» ወደ ሚሉት አላየህምን? በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲሆኑ ወደ ጣኦት መፋረድን ይፈልጋሉ:: ሰይጣንም ከእውነት የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ رَأَيْتَ ٱلْمُنَٰفِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودًا

Amharic Translation - Africa Academy61. ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው ቁርኣንና ወደ መልዕክተኛው ኑ።» በተባሉ ጊዜ አስመሳዮችን ካንተ በሀይል ሲሸሹ ታያቸዋለህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَيْفَ إِذَآ أَصَٰبَتْهُم مُّصِيبَةٌۢ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيهِمْ ثُمَّ جَآءُوكَ يَحْلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنْ أَرَدْنَآ إِلَّآ إِحْسَٰنًا وَتَوْفِيقًا

Amharic Translation - Africa Academy62. እጆቻቸዉም ባስቀደሙት ጥፋት ምክንያት መከራ በደረሰባቸውና ከዚያ «ደግን ሀሳብና ማስማማትን እንጂ ሌላን አልፈለግንም።» በማለት በአላህ የሚምሉ ሆነው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እንዴት ይሆናል?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَعْلَمُ ٱللَّهُ مَا فِى قُلُوبِهِمْ فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَعِظْهُمْ وَقُل لَّهُمْ فِىٓ أَنفُسِهِمْ قَوْلًۢا بَلِيغًا

Amharic Translation - Africa Academy63. እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው:: ከእነርሱ ራስህን አግልል:: ገስፃቸዉም:: ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ጠልቆ የሚገባ ጠንካራ ቃል ተናገራቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَلَوْ أَنَّهُمْ إِذ ظَّلَمُوٓا۟ أَنفُسَهُمْ جَآءُوكَ فَٱسْتَغْفَرُوا۟ ٱللَّهَ وَٱسْتَغْفَرَ لَهُمُ ٱلرَّسُولُ لَوَجَدُوا۟ ٱللَّهَ تَوَّابًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንንም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም:: እነርሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ መጥተው አላህን ምህረት በለመኑና መልዕክተኛዉም ለእነርሱ ምህረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ሆኖ ባገኙት ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም:: በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ የሚያስፈርዱህ ሆነው ከዚያ ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አማኝ አይሆኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ أَنَّا كَتَبْنَا عَلَيْهِمْ أَنِ ٱقْتُلُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ أَوِ ٱخْرُجُوا۟ مِن دِيَٰرِكُم مَّا فَعَلُوهُ إِلَّا قَلِيلٌ مِّنْهُمْ وَلَوْ أَنَّهُمْ فَعَلُوا۟ مَا يُوعَظُونَ بِهِۦ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ وَأَشَدَّ تَثْبِيتًا

Amharic Translation - Africa Academy66. እኛም በእነርሱ ላይ፡- «ነፍሶቻችሁን ግደሉ» ወይም «ከአገሮቻችሁ ውጡ» ማለትን በፃፍን ኖሮ ከእነርሱ ጥቂቶቹ እንጂ ባልሰሩት (ባልተገበሩት) ነበር። የሚገሰጹበትን ነገር በተገበሩት ኖሮ ለእነርሱ መልካምና በእምነታቸው ላይ ለመርጋትም በጣም የበረታ በሆነ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذًا لَّـَٔاتَيْنَٰهُم مِّن لَّدُنَّآ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy67. ያን ጊዜ ደግሞ ከእኛ ዘንድ ታላቅን ምንዳ በሰጠናቸው ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَهَدَيْنَٰهُمْ صِرَٰطًا مُّسْتَقِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy68. ቀጥተኛውንም መንገድ በእርግጥ በመራናቸው ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَعَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ وَٱلصِّدِّيقِينَ وَٱلشُّهَدَآءِ وَٱلصَّٰلِحِينَ وَحَسُنَ أُو۟لَٰٓئِكَ رَفِيقًا

Amharic Translation - Africa Academy69. አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ፀጋውን ከዋለላቸው ከነብያት፤ ከፃድቃን፤ ከሰማዕታትና ከመልካሞቹ ጋር ይሆናሉ። የእነዚያም ጓደኝነት አማረ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ ٱلْفَضْلُ مِنَ ٱللَّهِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy70. ይህ ችሮታ ከአላህ የተለገሰ ነው:: አዋቂነትም በአላህ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ خُذُوا۟ حِذْرَكُمْ فَٱنفِرُوا۟ ثُبَاتٍ أَوِ ٱنفِرُوا۟ جَمِيعًا

Amharic Translation - Africa Academy71. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ:: ክፍልፍልም ወይም በአንድ ሆናችሁ ለዘመቻ ውጡ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنَّ مِنكُمْ لَمَن لَّيُبَطِّئَنَّ فَإِنْ أَصَٰبَتْكُم مُّصِيبَةٌ قَالَ قَدْ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَىَّ إِذْ لَمْ أَكُن مَّعَهُمْ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy72. ከናንተ ውስጥ በእርግጥ ከዘመቻ ወደ ኋላ የሚንጓደድ (የሚጎተት) ሰው አለ:: አደጋም ካገኛችሁ «ከእነርሱ ጋር ተሳታፊ ባለመሆኔ አላህ በእኔ ላይ በእርግጥ ጸጋውን ዋለልኝ።» ይላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَئِنْ أَصَٰبَكُمْ فَضْلٌ مِّنَ ٱللَّهِ لَيَقُولَنَّ كَأَن لَّمْ تَكُنۢ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُۥ مَوَدَّةٌ يَٰلَيْتَنِى كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy73. ከአላህ የሆነ ችሮታ ካገኛችሁ ደግሞ በእናንተና በእርሱ መካከል ፍቅር አንዳልነበረ ሁኖ «ታላቅ እድል አገኝ ዘንድ ምን ነው ከእነርሱ ጋር በሆንኩ?» ይላል።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَلْيُقَٰتِلْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ يَشْرُونَ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا بِٱلْـَٔاخِرَةِ وَمَن يُقَٰتِلْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَيُقْتَلْ أَوْ يَغْلِبْ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy74. እናም እነዚያ ቅርቧን ህይወት በመጨረሻይቱ ሕይወት የሚለውጡ (የሚገዙ) በአላህ መንገድ ይጋደሉ:: በአላህ መንገድ የሚጋደልና ከዚያ የሚገደል ወይም የሚያሸንፍ ሁሉ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا لَكُمْ لَا تُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ ٱلرِّجَالِ وَٱلنِّسَآءِ وَٱلْوِلْدَٰنِ ٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَآ أَخْرِجْنَا مِنْ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةِ ٱلظَّالِمِ أَهْلُهَا وَٱجْعَل لَّنَا مِن لَّدُنكَ وَلِيًّا وَٱجْعَل لَّنَا مِن لَّدُنكَ نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy75. (አማኞች ሆይ!) በአላህ መንገድና ከወንዶች፣ ከሴቶችና ከልጆችም የሆኑትን እነዚያን፡- «ጌታችን ሆይ! ከዚህች ባለቤቶቿ በዳይ ከሆኑባት ከተማ አውጣን፤ ካንተም ዘንድ ለእኛ አሳዳሪን አድርግልን፤ ካንተ ዘንድም ለእኛ ረዳትን አድርግልን።» የሚሉትን ደካሞች ሰዎች ለማዳን የማትዋጉት ለምንድ ነው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱلطَّٰغُوتِ فَقَٰتِلُوٓا۟ أَوْلِيَآءَ ٱلشَّيْطَٰنِ إِنَّ كَيْدَ ٱلشَّيْطَٰنِ كَانَ ضَعِيفًا

Amharic Translation - Africa Academy76. እነዚያ ያመኑት በአላህ መንገድ ይዋጋሉ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ደግሞ በጣኦት መንገድ ይዋጋሉ:: እናም (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የሰይጣን ቡድኖችን ተፋለሙ:: የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ قِيلَ لَهُمْ كُفُّوٓا۟ أَيْدِيَكُمْ وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ فَلَمَّا كُتِبَ عَلَيْهِمُ ٱلْقِتَالُ إِذَا فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَخْشَوْنَ ٱلنَّاسَ كَخَشْيَةِ ٱللَّهِ أَوْ أَشَدَّ خَشْيَةً وَقَالُوا۟ رَبَّنَا لِمَ كَتَبْتَ عَلَيْنَا ٱلْقِتَالَ لَوْلَآ أَخَّرْتَنَآ إِلَىٰٓ أَجَلٍ قَرِيبٍ قُلْ مَتَٰعُ ٱلدُّنْيَا قَلِيلٌ وَٱلْـَٔاخِرَةُ خَيْرٌ لِّمَنِ ٱتَّقَىٰ وَلَا تُظْلَمُونَ فَتِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ለእነርሱ፡- «እጆቻችሁን ከመጋደል ሰብስቡ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፤ ግዴታ ምጽዋትን ስጡ።» ወደ ተባሉት አላየህምን? በእነርሱ ላይ መጋደል ግዴታ በሆነባቸው ጊዜ ደግሞ ከእነርሱ መካከል ከፊሎቹ ወዲያውኑ ሰዎችን ልክ አላህን እንደሚፈሩ ወይም የበለጠ ይፈራሉ:: «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መጋደልን ለምን ደነገግህ? እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አታቆየንም ኖሯልን?» ይላሉ:: «የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅም አነስተኛ ነው:: የመጨረሻይቱ ዓለም ጥቅም ግን አላህን ለሚፈራ ሁሉ በላጭ ነው። በተምር ፍሬ ውስጥ ያለችን ክር መሰል ያህል እንኳ አትበደሉም።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَيْنَمَا تَكُونُوا۟ يُدْرِككُّمُ ٱلْمَوْتُ وَلَوْ كُنتُمْ فِى بُرُوجٍ مُّشَيَّدَةٍ وَإِن تُصِبْهُمْ حَسَنَةٌ يَقُولُوا۟ هَٰذِهِۦ مِنْ عِندِ ٱللَّهِ وَإِن تُصِبْهُمْ سَيِّئَةٌ يَقُولُوا۟ هَٰذِهِۦ مِنْ عِندِكَ قُلْ كُلٌّ مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ فَمَالِ هَٰٓؤُلَآءِ ٱلْقَوْمِ لَا يَكَادُونَ يَفْقَهُونَ حَدِيثًا

Amharic Translation - Africa Academy78. የትም ስፍራ ብትሆኑ ሞት ያገኛችኋል:: በጠነከሩ ህንፃዎች ውስጥም ብትደብቁ እንኳን:: ደግ ነገር ካገኛቸው «ይህ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ:: መከራ ካገኛቸው ግን «ይህ ካንተ ዘንድ የመጣ ነው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም (ደጉም ክፉዉም) ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው።» በላቸው:: እነዚህ ሰዎች ንግግርን ሊረዱ የማይቀርቡት ለምንድን ነው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّآ أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ ٱللَّهِ وَمَآ أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ وَأَرْسَلْنَٰكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy79. (የሰው ልጅ ሆይ!) ደግ ነገር የሚያገኝህ ከአላህ ችሮታ ነው:: የሚደርስብህ መከራ ግን ከራስህ ጥፋት የተነሳ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለሰዎች ሁሉ መልዕክተኛ አድርገን ላክንህ:: መስካሪነትም በአላህ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّن يُطِعِ ٱلرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ ٱللَّهَ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا

Amharic Translation - Africa Academy80. መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ አላህን ታዘዘ:: ከትዕዛዝም የሸሸው ጉዳዩ አያሳስብህ:: በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَقُولُونَ طَاعَةٌ فَإِذَا بَرَزُوا۟ مِنْ عِندِكَ بَيَّتَ طَآئِفَةٌ مِّنْهُمْ غَيْرَ ٱلَّذِى تَقُولُ وَٱللَّهُ يَكْتُبُ مَا يُبَيِّتُونَ فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy81. አጠገብህ ሲሆኑ የአንተ ታዛዥ ነን ይላሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ከዚያ በአጠገብህ ከሚሉት ሌላን በልቦቻቸው ያሳድራሉ:: አላህ በልቦቻቸው የሚያሳድሩትን ነገር ሁሉ ይጽፋል:: ስለዚህ ተዋቸውና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: መመኪያነት አላህ ብቻ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلْقُرْءَانَ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ ٱللَّهِ لَوَجَدُوا۟ فِيهِ ٱخْتِلَٰفًا كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy82. ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ የመጣ በነበረ ኖሮ በውስጡ ብዙ መለያየትን ባገኙ ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا جَآءَهُمْ أَمْرٌ مِّنَ ٱلْأَمْنِ أَوِ ٱلْخَوْفِ أَذَاعُوا۟ بِهِۦ وَلَوْ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰٓ أُو۟لِى ٱلْأَمْرِ مِنْهُمْ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِينَ يَسْتَنۢبِطُونَهُۥ مِنْهُمْ وَلَوْلَا فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُۥ لَٱتَّبَعْتُمُ ٱلشَّيْطَٰنَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy83. ሰላምን ወይም ስጋትን የሚመለከት ወሬ በመጣላቸው ጊዜ እርሱን ያሰራጫሉ (ያጋንናሉ)። ወደ መልዕክተኛውና ከእነርሱ መካከል የጉዳይ ባለቤቶች ወደ ሆኑት አዋቂዎቹ በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ መካከል ነገሩን በትክክል የሚረዱት ክፍሎች ባወቁት ነበር:: በእናንተ ላይ የአላህን ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶቹ በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَقَٰتِلْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا تُكَلَّفُ إِلَّا نَفْسَكَ وَحَرِّضِ ٱلْمُؤْمِنِينَ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَكُفَّ بَأْسَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَٱللَّهُ أَشَدُّ بَأْسًا وَأَشَدُّ تَنكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ መንገድ ተዋጋ:: ራስህን እንጂ ሌላን አትገደድም:: አማኞችንም በአላህ መንገድ ላይ በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: አላህ የእነዚያን የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክል ይከጀላል:: አላህ በሃይል በመያዙ የበረታና ቅጣቱም የጠነከረ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّن يَشْفَعْ شَفَٰعَةً حَسَنَةً يَكُن لَّهُۥ نَصِيبٌ مِّنْهَا وَمَن يَشْفَعْ شَفَٰعَةً سَيِّئَةً يَكُن لَّهُۥ كِفْلٌ مِّنْهَا وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ مُّقِيتًا

Amharic Translation - Africa Academy85. መልካም መታደግን የሚታደግ (ሽምግልናን የሚሸመግል) ሰው ሁሉ ለራሱ ከእርሷ እድል ይኖረዋል:: መጥፎ መታደግንም የሚታደግ ሰው ለእርሱ ከእርሷ ድርሻ ይኖረዋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا۟ بِأَحْسَنَ مِنْهَآ أَوْ رُدُّوهَآ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ حَسِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy86.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሰላምታ በቀረበላችሁ ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታን መልሱ። ወይም እርሷኑ ራሷን መልሷት። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ ٱللَّهِ حَدِيثًا

Amharic Translation - Africa Academy87. አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላከ የለም:: ወደ ትንሳኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን በእርግጥ ይሰበስባችኋል:: በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَمَا لَكُمْ فِى ٱلْمُنَٰفِقِينَ فِئَتَيْنِ وَٱللَّهُ أَرْكَسَهُم بِمَا كَسَبُوٓا۟ أَتُرِيدُونَ أَن تَهْدُوا۟ مَنْ أَضَلَّ ٱللَّهُ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy88.(አማኞች ሆይ) አላህ በስራዎቻቸው ምክንያት ወደ ክህደት የመለሳቸው ሲሆኑ በሙናፊቆች ጉዳይ እናንተ ለሁለት ቡድን የተከፈላችሁት ምን ሆናችሁ ነው? አላህ ያጠመመውን ሰው ልታቀኑ ታስባላችሁን? (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያጠመመውን ሰው ለእርሱ መንገድ ፈጽሞ አታገኝለትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَدُّوا۟ لَوْ تَكْفُرُونَ كَمَا كَفَرُوا۟ فَتَكُونُونَ سَوَآءً فَلَا تَتَّخِذُوا۟ مِنْهُمْ أَوْلِيَآءَ حَتَّىٰ يُهَاجِرُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَخُذُوهُمْ وَٱقْتُلُوهُمْ حَيْثُ وَجَدتُّمُوهُمْ وَلَا تَتَّخِذُوا۟ مِنْهُمْ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy89. (አማኞች ሆይ) በአላህ እንደ ካዱ ሁሉ እናንተም እንድትክዱና ከእነርሱ ጋር እኩል እንድትሆኑ ተመኙ:: በአላህ መንገድ እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ መካከል ወዳጆችን አትያዙ:: ከእምነት ካፈገፈጉም ማርኳቸው:: ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ከእነርሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلَّذِينَ يَصِلُونَ إِلَىٰ قَوْمٍۭ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَٰقٌ أَوْ جَآءُوكُمْ حَصِرَتْ صُدُورُهُمْ أَن يُقَٰتِلُوكُمْ أَوْ يُقَٰتِلُوا۟ قَوْمَهُمْ وَلَوْ شَآءَ ٱللَّهُ لَسَلَّطَهُمْ عَلَيْكُمْ فَلَقَٰتَلُوكُمْ فَإِنِ ٱعْتَزَلُوكُمْ فَلَمْ يُقَٰتِلُوكُمْ وَأَلْقَوْا۟ إِلَيْكُمُ ٱلسَّلَمَ فَمَا جَعَلَ ٱللَّهُ لَكُمْ عَلَيْهِمْ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy90. እነዚያ በእናተና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ወዳላቸው ህዝቦች የሚጠጉ፤ ወይም እናንተን ለመጋደልም ይሁን ወገኖቻቸውን ለመጋደል ልቦቻቸው የተጨነቁ ሆነው ወደ እናንተ የመጡ ሲቀሩ እነዚያንማ አትጋደሏቸው:: አላህ በፈለገ ኖሮ በእናንተ ላይ ሀይል በሰጣቸውና በተዋጓችሁ ነበር:: ቢተዋችሁ ባይዋጓችሁ ወደ እናንተ የእርቅን ሀሳብ ቢያቀርቡ አላህ ለእናንተ በእነርሱ ላይ የመዋጋት መንገድን አላደረገም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَتَجِدُونَ ءَاخَرِينَ يُرِيدُونَ أَن يَأْمَنُوكُمْ وَيَأْمَنُوا۟ قَوْمَهُمْ كُلَّ مَا رُدُّوٓا۟ إِلَى ٱلْفِتْنَةِ أُرْكِسُوا۟ فِيهَا فَإِن لَّمْ يَعْتَزِلُوكُمْ وَيُلْقُوٓا۟ إِلَيْكُمُ ٱلسَّلَمَ وَيَكُفُّوٓا۟ أَيْدِيَهُمْ فَخُذُوهُمْ وَٱقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ وَأُو۟لَٰٓئِكُمْ جَعَلْنَا لَكُمْ عَلَيْهِمْ سُلْطَٰنًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy91. ከናንተም ሆነ ከወገኖቻቸው ለመዳን የሚፈልጉ ሌሎች ቡድኖችም ታገኛላችሁ:: ወደ እውከት እንዲመለሱ በተጠሩ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይዘፈቃሉ:: ባይተዋችሁና እርቅን ካላቀረቡላችሁ እጆቻቸውንም ባይሰበስቡ ባገኛችኋቸው ስፍራ ሁሉ ማርኳቸው:: ግደሏቸዉም:: እነዚያን ለእናንተ በእነርሱ ላይ ግልጽ ማስረጃን አድርገንላችኋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ أَن يَقْتُلَ مُؤْمِنًا إِلَّا خَطَـًٔا وَمَن قَتَلَ مُؤْمِنًا خَطَـًٔا فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُّؤْمِنَةٍ وَدِيَةٌ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰٓ أَهْلِهِۦٓ إِلَّآ أَن يَصَّدَّقُوا۟ فَإِن كَانَ مِن قَوْمٍ عَدُوٍّ لَّكُمْ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُّؤْمِنَةٍ وَإِن كَانَ مِن قَوْمٍۭ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَٰقٌ فَدِيَةٌ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰٓ أَهْلِهِۦ وَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُّؤْمِنَةٍ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ تَوْبَةً مِّنَ ٱللَّهِ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy92. አማኝ በስህተት ካልሆነ በስተቀር አማኝን መግደል አይገባዉም:: አማኝን በስህተት የገደለም አማኝ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ምህረት ካላደረጉለት በስተቀር ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማ መክፈል አለበት:: ተገዳዩ ምዕመን ሆኖ ለእናንተ ጠላት ከሆኑ ህዝቦች ዘንድ ቢሆንም አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ተገዳዩ በእናንተ እና በእነርሱ መካከል ቃል ኪዳን ካላቸዉም ህዝቦች ጋር ቢሆን ለቤተሰቦቹ የምትሰጥ ጉማና አማኝን ባሪያ ነፃ ማውጣት አለበት:: ይህንን ያላገኘም በተከታታይ ሁለት ወሮችን መፆም አለበት:: ከአላህ የሆነ ጸጸት (ለመቀበል ደነገገላችሁ::) አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَقْتُلْ مُؤْمِنًا مُّتَعَمِّدًا فَجَزَآؤُهُۥ جَهَنَّمُ خَٰلِدًا فِيهَا وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ وَلَعَنَهُۥ وَأَعَدَّ لَهُۥ عَذَابًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy93. አማኝን አስቦ የሚገድል ቅጣቱ በውስጧ ዘወታሪ ሲሆን ገሀነም ናት:: አላህ በእርሱ ላይ ተቆጣ:: ረገመዉም:: ለእርሱ ከባድ ቅጣትን አዘጋጀቶለታል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا ضَرَبْتُمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ فَتَبَيَّنُوا۟ وَلَا تَقُولُوا۟ لِمَنْ أَلْقَىٰٓ إِلَيْكُمُ ٱلسَّلَٰمَ لَسْتَ مُؤْمِنًا تَبْتَغُونَ عَرَضَ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا فَعِندَ ٱللَّهِ مَغَانِمُ كَثِيرَةٌ كَذَٰلِكَ كُنتُم مِّن قَبْلُ فَمَنَّ ٱللَّهُ عَلَيْكُمْ فَتَبَيَّنُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy94. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ለመዋጋት በተጓዛችሁ ጊዜ አረጋግጡ:: ሰላምታን ወደ እናንተ ላቀረበ ሰው የቅርቢቱን ሕይወት ጥቅም የምትፈልጉ ሆናችሁ «ትክክለኛ አማኝ አይደለህም።» አትበሉት:: አላህ ዘንድ ብዙ ምርኮዎች አሉና:: እናንተም ከዚህ በፊት ልክ እንደዚሁ ነበራችሁ:: አላህ በእናንተ ላይ ለገሰ:: ስለዚህም አረጋግጡ:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يَسْتَوِى ٱلْقَٰعِدُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ غَيْرُ أُو۟لِى ٱلضَّرَرِ وَٱلْمُجَٰهِدُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلْمُجَٰهِدِينَ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ عَلَى ٱلْقَٰعِدِينَ دَرَجَةً وَكُلًّا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلْحُسْنَىٰ وَفَضَّلَ ٱللَّهُ ٱلْمُجَٰهِدِينَ عَلَى ٱلْقَٰعِدِينَ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy95. ከአማኞች የጉዳት ባለቤት ከሆኑት በስተቀር ተቀማጮቹ እና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉት አይስተካከሉም:: በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም የሚታገሉትን አላህ በተቀማጮቹ ላይ በደረጃ አበለጠ:: ለሁሉም አላህ መልካሚቱን (ገነት) ተስፋ ሰጠ (ቃል ኪዳን ገባ):: ታጋዮቹንም በተቀማጮቹ ላይ አላህ በታላቅ ምንዳ አበለጠ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

دَرَجَٰتٍ مِّنْهُ وَمَغْفِرَةً وَرَحْمَةً وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy96. ከእርሱ ዘንድ በሆኑ ደረጃዎች አበለጠ:: ምህረትንም አደረገ:: እዝነትንም አዘነላቸው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ تَوَفَّىٰهُمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِىٓ أَنفُسِهِمْ قَالُوا۟ فِيمَ كُنتُمْ قَالُوا۟ كُنَّا مُسْتَضْعَفِينَ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ أَلَمْ تَكُنْ أَرْضُ ٱللَّهِ وَٰسِعَةً فَتُهَاجِرُوا۟ فِيهَا فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَسَآءَتْ مَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy97. እነዚያ ለእምነት ሲሉ ባለመሰደድ ነፍሶቻቸውን በዳዮች ሆነው መላዕክት የገደሏቸው መላዕክት ለእነርሱ «በምን ነገር ላይ ነበራችሁ?» ይሏቸዋል። «በምድር ውስጥ ደካሞች ነበርን።» ይላሉ:: «የአላህ ምድር ትሰደዱባት ዘንድ ሰፊ አልነበረችምን?» ይሏቸዋል። እነዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ገሀነምም መመለሻነቷ ከፋች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ ٱلرِّجَالِ وَٱلنِّسَآءِ وَٱلْوِلْدَٰنِ لَا يَسْتَطِيعُونَ حِيلَةً وَلَا يَهْتَدُونَ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy98. ከወንዶችና ከሴቶች ከህፃኖችም ሲሆኑ ከሀገራቸው ለመውጣት መላን የማይችሉና መንገድንም የማይመሩ ደካሞች ባለመሰደዳቸው ግን ምንም ቅጣት የለባቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأُو۟لَٰٓئِكَ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَعْفُوَ عَنْهُمْ وَكَانَ ٱللَّهُ عَفُوًّا غَفُورًا

Amharic Translation - Africa Academy99. እነዚያ አላህ ከእነርሱ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል:: አላህም ይቅር ባይና መሀሪ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يُهَاجِرْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ يَجِدْ فِى ٱلْأَرْضِ مُرَٰغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً وَمَن يَخْرُجْ مِنۢ بَيْتِهِۦ مُهَاجِرًا إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ ثُمَّ يُدْرِكْهُ ٱلْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy100. በአላህ መንገድ የሚሰደድ ሁሉ በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል:: ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ስደተኛ ሆኖ ከቤቱ የሚወጣና ከዚያ በመንገድ ላይ ሞት የሚያገኘው ምንዳው በእርግጥ በአላህ ዘንድ ተረጋገጠ:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا ضَرَبْتُمْ فِى ٱلْأَرْضِ فَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَن تَقْصُرُوا۟ مِنَ ٱلصَّلَوٰةِ إِنْ خِفْتُمْ أَن يَفْتِنَكُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنَّ ٱلْكَٰفِرِينَ كَانُوا۟ لَكُمْ عَدُوًّا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy101.(አማኞች) በምድር ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ሊያውኳችሁ እንደሆነ ብትፈሩ ከሶላቶች መካከል ከፊሎችን (ባለ አራት አራት ረካአ የሆኑትን ቁጥራቸውን ወደ ሁለት ሁለት በመቀነስ) ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለም። ከሓዲያን ለእናንተ በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸውና።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا كُنتَ فِيهِمْ فَأَقَمْتَ لَهُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَلْتَقُمْ طَآئِفَةٌ مِّنْهُم مَّعَكَ وَلْيَأْخُذُوٓا۟ أَسْلِحَتَهُمْ فَإِذَا سَجَدُوا۟ فَلْيَكُونُوا۟ مِن وَرَآئِكُمْ وَلْتَأْتِ طَآئِفَةٌ أُخْرَىٰ لَمْ يُصَلُّوا۟ فَلْيُصَلُّوا۟ مَعَكَ وَلْيَأْخُذُوا۟ حِذْرَهُمْ وَأَسْلِحَتَهُمْ وَدَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْ تَغْفُلُونَ عَنْ أَسْلِحَتِكُمْ وَأَمْتِعَتِكُمْ فَيَمِيلُونَ عَلَيْكُم مَّيْلَةً وَٰحِدَةً وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن كَانَ بِكُمْ أَذًى مِّن مَّطَرٍ أَوْ كُنتُم مَّرْضَىٰٓ أَن تَضَعُوٓا۟ أَسْلِحَتَكُمْ وَخُذُوا۟ حِذْرَكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ أَعَدَّ لِلْكَٰفِرِينَ عَذَابًا مُّهِينًا

Amharic Translation - Africa Academy102.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) በጦርነት ላይ በመካከላቸው በሆንክና ሶላትን ለእነርሱ ባሰገድካቸው ጊዜ ከእነርሱ አንዱ ቡድን ካንተ ጋር ይቁም:: መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: ሱጁድ ባደረጉ ጊዜ ከበስተኋላችሁ ይሁኑ:: ከዚያም እነዚያ ቡድኖች ወደ ግንባር ይሂዱና ያልሰገዱት ሌሎች ቡድኖች ይምጡ :: ከዚያም ካንተ ጋር ይስገዱ:: ጥንቃቄያቸውንና መሳሪያዎቻቸውንም ይያዙ:: እነዚያ በአላህ የካዱት ከትጥቅና ስንቃችሁ ብትዘናጉና በአንድ ጊዜ ቢወሯችሁ ይመኛሉ:: ዝናብ አውኳችሁ ወይም በሽተኛ ሆናችሁ ትጥቃችሁን ብታስቀምጡ በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: ጥንቃቄ አድርጉ:: አላህ ለካሐዲያን ሁሉ አዋራጅን ቅጣት አዘጋጀ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا قَضَيْتُمُ ٱلصَّلَوٰةَ فَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ قِيَٰمًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِكُمْ فَإِذَا ٱطْمَأْنَنتُمْ فَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتْ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ كِتَٰبًا مَّوْقُوتًا

Amharic Translation - Africa Academy103. ሶላትንም በፈጸማችሁ (በጨረሳችሁ) ጊዜ ቆማችሁ፣ ተቀምጣችሁና በጎኖቻችሁም ተጋድማችሁ አላህን አውሱ:: በተረጋጋችሁ ጊዜ ግን ሶላትን ደንቧን አሟልታችሁ ስገዱ:: ሶላት በአማኞች ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَهِنُوا۟ فِى ٱبْتِغَآءِ ٱلْقَوْمِ إِن تَكُونُوا۟ تَأْلَمُونَ فَإِنَّهُمْ يَأْلَمُونَ كَمَا تَأْلَمُونَ وَتَرْجُونَ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا يَرْجُونَ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy104.ሰዎቹንም ከመፈለግ አትስነፉ:: ስትቆስሉ የምትታመሙ ብትሆኑም እናንተ እንደምትታመሙ ሁሉ እነርሱም ይታመማሉ:: እናንተ ግን እነርሱ የማይከጅሉትን ከአላህ ትከጅላላችሁ:: አላህም ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ لِتَحْكُمَ بَيْنَ ٱلنَّاسِ بِمَآ أَرَىٰكَ ٱللَّهُ وَلَا تَكُن لِّلْخَآئِنِينَ خَصِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy105. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን:: እናም ለከዳተኞች ተከራካሪ አትሁን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱسْتَغْفِرِ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህን ምህረት ለምነው:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تُجَٰدِلْ عَنِ ٱلَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنفُسَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy107. ለእነዚያ ነፍሶቻቸውን ስለሚያታልሉት ሰዎች አትከራከር:: አላህ ከዳተኛንና ኃጢአተኛን ሰው አይወድምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْتَخْفُونَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَلَا يَسْتَخْفُونَ مِنَ ٱللَّهِ وَهُوَ مَعَهُمْ إِذْ يُبَيِّتُونَ مَا لَا يَرْضَىٰ مِنَ ٱلْقَوْلِ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطًا

Amharic Translation - Africa Academy108. ከሰው ይደበቃሉ:: አላህ በዕውቀቱ ከእነርሱ ጋር ሲሆን ከንግግር የማይወደውን ነገር በልቦቻቸው በሚያሳድሩ ጊዜ ከእርሱ አይደበቁም:: አላህ በሚሰሩት ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هَٰٓأَنتُمْ هَٰٓؤُلَآءِ جَٰدَلْتُمْ عَنْهُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا فَمَن يُجَٰدِلُ ٱللَّهَ عَنْهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ أَم مَّن يَكُونُ عَلَيْهِمْ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy109. እነሆ እናንተ እነዚያ በቅርቢቱ ሕይወት ውስጥ ከእነርሱ ተከራከራችሁ:: በትንሳኤ ቀን አላህን ስለ እነርሱ የሚከራከርላቸው ማን ነው? ወይስ ለእነርሱ ሀላፊ የሚሆን ማን ነው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَعْمَلْ سُوٓءًا أَوْ يَظْلِمْ نَفْسَهُۥ ثُمَّ يَسْتَغْفِرِ ٱللَّهَ يَجِدِ ٱللَّهَ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy110. መጥፎ ነገር የሚሰራ ወይም ነፍሱን የሚበድልና ከዚያም ተጸጽቶ አላህን ምህረት የሚለምን ሁሉ አላህን መሀሪና አዛኝ ሆኖ ያገኘዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَكْسِبْ إِثْمًا فَإِنَّمَا يَكْسِبُهُۥ عَلَىٰ نَفْسِهِۦ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy111. ኃጢአት የሚሰራም የሚሰራው ጥፋት ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَكْسِبْ خَطِيٓـَٔةً أَوْ إِثْمًا ثُمَّ يَرْمِ بِهِۦ بَرِيٓـًٔا فَقَدِ ٱحْتَمَلَ بُهْتَٰنًا وَإِثْمًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy112. ኃጢአትን ወይም ወንጀልን የሚሰራና ከዚያም በእርሱ ንጹህን የሚሰድብ ቅጥፈትንና ግልጽ ኃጢአትን በቁርጥ ተሸከመ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْلَا فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ وَرَحْمَتُهُۥ لَهَمَّت طَّآئِفَةٌ مِّنْهُمْ أَن يُضِلُّوكَ وَمَا يُضِلُّونَ إِلَّآ أَنفُسَهُمْ وَمَا يَضُرُّونَكَ مِن شَىْءٍ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy113. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባንተ ላይ ባልነበረ ኖሮ ከእነርሱ የሆነ ቡድኖች ሊያሳስቱህ ባሰቡ ነበር:: ነፍሶቻቸውን እንጂ ሌላ አያሳስቱም:: በምንም አይጎዱህም:: አላህ ባንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ:: የማታውቀውን ሁሉ አስተማረህ:: የአላህ ችሮታ ባንተ ላይ ታላቅ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا خَيْرَ فِى كَثِيرٍ مِّن نَّجْوَىٰهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَٰحٍۭ بَيْنَ ٱلنَّاسِ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ٱبْتِغَآءَ مَرْضَاتِ ٱللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy114. ከውይይቶቻቸው መካከል በምጽዋት ወይም በበጎ ስራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውይይት ውስጥ ደግ ነገር የለበትም:: ይህንንም የተባለውን የአላህን ውዴታ በመፈለግ ለሚሰራ ሁሉ ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يُشَاقِقِ ٱلرَّسُولَ مِنۢ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ ٱلْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ ٱلْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِۦ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِۦ جَهَنَّمَ وَسَآءَتْ مَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy115. ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለጸት በኋላ መልዕክተኛውን የሚቃረንና ከምዕመናኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሁሉ በመረጠው ጥመት ላይ እንተወዋለን። ወደ ገሀነምም እናስገባዋለን:: መመለሻይቱም ገሀነም ከፋች።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِۦ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُ وَمَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَٰلًۢا بَعِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy116. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከሽርክ በታች (ሌላ) ያለውን ጥፋት ግን ለሚሻው ይምራል:: በአላህ የሚያጋራም ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦٓ إِلَّآ إِنَٰثًا وَإِن يَدْعُونَ إِلَّا شَيْطَٰنًا مَّرِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy117. ከእርሱ ሌላ እንስት ጣኦታትን እንጂ አይገዙም:: አመጸኞች ሰይጣንንም እንጂ ሌላን አይገዙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّعَنَهُ ٱللَّهُ وَقَالَ لَأَتَّخِذَنَّ مِنْ عِبَادِكَ نَصِيبًا مَّفْرُوضًا

Amharic Translation - Africa Academy118. አላህም የረገመውን (እንዲህ) ያለውንም ሰይጣን እንጂ አይከተሉም: «ከባሮችህ የተወሰነን ድርሻ በእርግጥ እይዛለሁ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَأُضِلَّنَّهُمْ وَلَأُمَنِّيَنَّهُمْ وَلَـَٔامُرَنَّهُمْ فَلَيُبَتِّكُنَّ ءَاذَانَ ٱلْأَنْعَٰمِ وَلَـَٔامُرَنَّهُمْ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلْقَ ٱللَّهِ وَمَن يَتَّخِذِ ٱلشَّيْطَٰنَ وَلِيًّا مِّن دُونِ ٱللَّهِ فَقَدْ خَسِرَ خُسْرَانًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy119. «በእርግጥ አጠማቸዋለሁ:: ከንቱን ምኞትም አስመኛቸዋለሁ:: አዛቸዉምና የእንስሶችን ጀሮዎች ይተለትላሉ:: አዛቸዉምና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ።» (ያለውን ይከተላሉ።) ከአላህ ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ግልጽ ኪሳራን በእርግጥ ከሰረ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَعِدُهُمْ وَيُمَنِّيهِمْ وَمَا يَعِدُهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ إِلَّا غُرُورًا

Amharic Translation - Africa Academy120. የማይፈጽመውን ከንቱ ተስፋ ይሰጣቸዋል:: ያስመኛቸዋልም:: ሰይጣን ለማታለል እንጂ ቃል አይገባላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ مَأْوَىٰهُمْ جَهَنَّمُ وَلَا يَجِدُونَ عَنْهَا مَحِيصًا

Amharic Translation - Africa Academy121. እነዚያ የመጨረሻ መኖሪያቸው ገሀነም ናት:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا وَعْدَ ٱللَّهِ حَقًّا وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ ٱللَّهِ قِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy122. እነዚያ በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ እናስገባቸዋለን:: አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው:: በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّيْسَ بِأَمَانِيِّكُمْ وَلَآ أَمَانِىِّ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ مَن يَعْمَلْ سُوٓءًا يُجْزَ بِهِۦ وَلَا يَجِدْ لَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy123. ነገሩ በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም:: መጥፎን የሚሰራ ሁሉ በእርሱ ይመነዳል:: ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂን ረዳትንም አያገኝም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن يَعْمَلْ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُو۟لَٰٓئِكَ يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy124. ከወንድ ወይም ከሴት አማኝ ሆነው ከበጎ ስራዎች አንድንም ነገር የሚሰሩ ገነት ይገባሉ:: በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳን አይበደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُۥ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَٱتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَٰهِيمَ حَنِيفًا وَٱتَّخَذَ ٱللَّهُ إِبْرَٰهِيمَ خَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy125. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን አለ? አላህ ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጎ ያዘው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ مُّحِيطًا

Amharic Translation - Africa Academy126. በሰማያትና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአላህ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ በእውቀት ከባቢ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَسْتَفْتُونَكَ فِى ٱلنِّسَآءِ قُلِ ٱللَّهُ يُفْتِيكُمْ فِيهِنَّ وَمَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فِى ٱلْكِتَٰبِ فِى يَتَٰمَى ٱلنِّسَآءِ ٱلَّٰتِى لَا تُؤْتُونَهُنَّ مَا كُتِبَ لَهُنَّ وَتَرْغَبُونَ أَن تَنكِحُوهُنَّ وَٱلْمُسْتَضْعَفِينَ مِنَ ٱلْوِلْدَٰنِ وَأَن تَقُومُوا۟ لِلْيَتَٰمَىٰ بِٱلْقِسْطِ وَمَا تَفْعَلُوا۟ مِنْ خَيْرٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِهِۦ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) ስለ ሴቶች ጉዳይ ይጠይቁሃል። «አላህ ስለነሱ ይነግራችኋል:: ያም በመጽሐፍ ውስጥ በእናንተ ላይ የሚነበበው ሲሆን በእነዚያ ከውርስ የተደነገገላቸውን ድርሻ በማትሰጧቸው ሴቶችና ልታገቧቸው በማትፈልጉት የቲሞች ሴቶች ይህንን እንዳታደርጉ፤ ህፃናት ለሆኑትም ደካሞች መብታቸውን እንድትሰጡ፤ ለየቲሞች በትክክል እንድትቆሙ ይነገራችኋል።» በላቸው:: ከበጎም ስራ የሆነን ማንኛውንም ስራ ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِنِ ٱمْرَأَةٌ خَافَتْ مِنۢ بَعْلِهَا نُشُوزًا أَوْ إِعْرَاضًا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَآ أَن يُصْلِحَا بَيْنَهُمَا صُلْحًا وَٱلصُّلْحُ خَيْرٌ وَأُحْضِرَتِ ٱلْأَنفُسُ ٱلشُّحَّ وَإِن تُحْسِنُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy128. ሴት ልጅ ከባሏ ጥላቻን ወይም ከእርሷ ፊቱን ማዞሩን ብታውቅ እና ከዚያ በመካከላቸው እንደገና ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኃጢአት የለባቸዉም:: መታረቅ መልካም ነውና:: ነፍሶች ሁሉ ንፍገት ተጣለባቸው:: (ባሎች ሆይ!) መልካም ነገር ብትሰሩና ብትጠነቀቁ ግን አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَن تَسْتَطِيعُوٓا۟ أَن تَعْدِلُوا۟ بَيْنَ ٱلنِّسَآءِ وَلَوْ حَرَصْتُمْ فَلَا تَمِيلُوا۟ كُلَّ ٱلْمَيْلِ فَتَذَرُوهَا كَٱلْمُعَلَّقَةِ وَإِن تُصْلِحُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy129. (ባሎች ሆይ! ) በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ በፍቅር ለማስተካከል አትችሉም። ሆኖም እንደተንጠለጠለች (ገመድ) አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ ወደምትወዷት ሴት ሙሉ መዘንበልን አትንዘንበሉ:: ብታበጁና ብትጠነቀቁ አላህ መሀሪና አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن يَتَفَرَّقَا يُغْنِ ٱللَّهُ كُلًّا مِّن سَعَتِهِۦ وَكَانَ ٱللَّهُ وَٰسِعًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy130. ባልና ሚስት በመሀከላቸው በተፈጠረው ችግር ቢለያዩ አላህ ሁሉንም በችሮታው ያብቃቃቸዋል:: አላህ ችሮታው ሰፊና ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَلَقَدْ وَصَّيْنَا ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ وَإِيَّاكُمْ أَنِ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَإِن تَكْفُرُوا۟ فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَكَانَ ٱللَّهُ غَنِيًّا حَمِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy131. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያንም ከበፊታችሁ መጽሐፍ የተሰጡትን እናንተንም አላህን ፍሩ በማለት በእርግጥ አዘዝን:: ብትክዱም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው አትጎዱትም:: አላህ በራሱ ተብቃቂና ምስጉን ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy132. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: መመኪያነትም በአላህ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ أَيُّهَا ٱلنَّاسُ وَيَأْتِ بِـَٔاخَرِينَ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ ذَٰلِكَ قَدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy133. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) አላህ ቢሻ ያስወግዳችሁና ሌሎችን በቦታችሁ ላይ ይተካል:: አላህም በዚህ ላይ ቻይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّن كَانَ يُرِيدُ ثَوَابَ ٱلدُّنْيَا فَعِندَ ٱللَّهِ ثَوَابُ ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَكَانَ ٱللَّهُ سَمِيعًۢا بَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy134. የቅርቢቱን አለም ምንዳ የሚፈልግ ሁሉ አላህ ዘንድ የቅርቢቱና የመጨረሻይቱ ምንዳ አለ:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّٰمِينَ بِٱلْقِسْطِ شُهَدَآءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰٓ أَنفُسِكُمْ أَوِ ٱلْوَٰلِدَيْنِ وَٱلْأَقْرَبِينَ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَٱللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا فَلَا تَتَّبِعُوا۟ ٱلْهَوَىٰٓ أَن تَعْدِلُوا۟ وَإِن تَلْوُۥٓا۟ أَوْ تُعْرِضُوا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy135. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በነፍሶቻችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢሆንም እንኳ በትክክል ለፍትህ ቋሚዎች ለአላህ መስካሪዎች ሁኑ:: ሀብታም ወይም ድሃ ቢሆንም አላህ ከእነርሱ ለእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው:: እንዳታዳሉም ዝንባሌን አትከተሉ:: ምስክርን ብታጣምሙ ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሰሩት ነገር ላይ ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِى نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِن قَبْلُ وَمَن يَكْفُرْ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَٰلًۢا بَعِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy136. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልዕክተኛው በዚያ በመልዕክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍም ከዚያ በፊትም ባወረደው መጽሐፍ እመኑ:: በአላህ፣ በመላዕክቱ፣ በመጽሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹና በመጨረሻውም ቀን የካደ ሁሉ ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ثُمَّ كَفَرُوا۟ ثُمَّ ءَامَنُوا۟ ثُمَّ كَفَرُوا۟ ثُمَّ ٱزْدَادُوا۟ كُفْرًا لَّمْ يَكُنِ ٱللَّهُ لِيَغْفِرَ لَهُمْ وَلَا لِيَهْدِيَهُمْ سَبِيلًۢا

Amharic Translation - Africa Academy137. እነዚያ ያመኑና ከዚያም የካዱ ከዚያም ያመኑ ከዚያም የካዱ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ አላህ ለእነርሱ የሚምራቸውና ቅኑን መንገድም የሚመራቸው አይደሉም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَشِّرِ ٱلْمُنَٰفِقِينَ بِأَنَّ لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy138. አስመሳዮችን ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት ያላቸው መሆኑን አብስራቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَتَّخِذُونَ ٱلْكَٰفِرِينَ أَوْلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلْمُؤْمِنِينَ أَيَبْتَغُونَ عِندَهُمُ ٱلْعِزَّةَ فَإِنَّ ٱلْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا

Amharic Translation - Africa Academy139. እነዚያ ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ ሰዎች እነርሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን? ልቅና ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلْكِتَٰبِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا۟ مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا۟ فِى حَدِيثٍ غَيْرِهِۦٓ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ جَامِعُ ٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱلْكَٰفِرِينَ فِى جَهَنَّمَ جَمِيعًا

Amharic Translation - Africa Academy140. በእናንተ ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አናቅጽ በእርሷ ሲካድባት በእርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ:: እናንተ ያን ጊዜ ቢጤያቸው ናችሁና:: አላህ አስመሳዮችንም ከሓዲያንንም በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱلَّذِينَ يَتَرَبَّصُونَ بِكُمْ فَإِن كَانَ لَكُمْ فَتْحٌ مِّنَ ٱللَّهِ قَالُوٓا۟ أَلَمْ نَكُن مَّعَكُمْ وَإِن كَانَ لِلْكَٰفِرِينَ نَصِيبٌ قَالُوٓا۟ أَلَمْ نَسْتَحْوِذْ عَلَيْكُمْ وَنَمْنَعْكُم مِّنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ فَٱللَّهُ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ وَلَن يَجْعَلَ ٱللَّهُ لِلْكَٰفِرِينَ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy141. እነዚያ (አስመሳዮች) በእናንተ ላይ የጊዜ መዘዋወርን የሚጠባበቁ ናቸው:: ለእናንተም ከአላህ የሆነ አሸናፊነት ሲኖራችሁ «ከናንተ ጋር አልነበርንምን?» ይላሉ:: ለከሓዲያን እድል ሲኖር ደግሞ «ከአሁን በፊት እኛ በእናንተ ላይ አልተሾምንባችሁምና (አልተውናችሁምን?) ከአማኞች አደጋስ አልከለከልናችሁምን?» ይላሉ:: አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ ይፈርዳል:: አላህ ለከሓዲያን በአማኞች ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ يُخَٰدِعُونَ ٱللَّهَ وَهُوَ خَٰدِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوٓا۟ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ قَامُوا۟ كُسَالَىٰ يُرَآءُونَ ٱلنَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ ٱللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy142. አስመሳዮች አላህን ያታልላሉ:: እርሱም አታላያቸው ነው:: ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾችና ሰዎችን የሚያሳዩ ሆነው ይቆማሉ:: አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّذَبْذَبِينَ بَيْنَ ذَٰلِكَ لَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ وَلَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy143. በዚህ መካከል ወላዋዮች ሆነው ይታያሉ:: ወደ እነዚህም ወደ እነዚያም አይደሉም:: አላህም ያሳሳተውን ለእርሱ የቅንነት መንገድን በፍጹም አታገኝለትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ ٱلْكَٰفِرِينَ أَوْلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلْمُؤْمِنِينَ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا۟ لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَٰنًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy144. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ:: ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ فِى ٱلدَّرْكِ ٱلْأَسْفَلِ مِنَ ٱلنَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በእርግጥ ከእሳት በታችኛዋ አዘቅት ውስጥ ናቸው:: እናም ለእነርሱ ረዳትን አታገኝላቸዉም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُوا۟ وَأَصْلَحُوا۟ وَٱعْتَصَمُوا۟ بِٱللَّهِ وَأَخْلَصُوا۟ دِينَهُمْ لِلَّهِ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَعَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَسَوْفَ يُؤْتِ ٱللَّهُ ٱلْمُؤْمِنِينَ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy146. እነዚያ የተመለሱና ስራቸውን ያሳመሩ በአላህ የተጠበቁ ሃይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉት ሲቀሩ:: እነዚያስ ከአማኞች ጋር ናቸው:: ለአማኞችም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّا يَفْعَلُ ٱللَّهُ بِعَذَابِكُمْ إِن شَكَرْتُمْ وَءَامَنتُمْ وَكَانَ ٱللَّهُ شَاكِرًا عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy147. ብታመሰግኑና ብታምኑ አላህ እናንተን በመቅጣት ምን ያደርጋል? አላህም ወረታን መላሽ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّا يُحِبُّ ٱللَّهُ ٱلْجَهْرَ بِٱلسُّوٓءِ مِنَ ٱلْقَوْلِ إِلَّا مَن ظُلِمَ وَكَانَ ٱللَّهُ سَمِيعًا عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy148. አላህ በክፉ ንግግር መጮህን ከተበደለ ሰው ጩኸት በስተቀር አይወድም:: አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِن تُبْدُوا۟ خَيْرًا أَوْ تُخْفُوهُ أَوْ تَعْفُوا۟ عَن سُوٓءٍ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّا قَدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy149. ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር (በደል) ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ እና ቻይ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكْفُرُونَ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَيُرِيدُونَ أَن يُفَرِّقُوا۟ بَيْنَ ٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَيَقُولُونَ نُؤْمِنُ بِبَعْضٍ وَنَكْفُرُ بِبَعْضٍ وَيُرِيدُونَ أَن يَتَّخِذُوا۟ بَيْنَ ذَٰلِكَ سَبِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy150. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ የሚክዱ፤ በአላህና በመልዕክተኞቹም መካከል መለየትን የሚፈልጉና «በከፊሉ እናምናለን በከፊሉ ደግሞ እንክዳለን» የሚሉ ሁሉ በዚህ መካከል መንገድን ሊይዙ የሚፈልጉ፣

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْكَٰفِرُونَ حَقًّا وَأَعْتَدْنَا لِلْكَٰفِرِينَ عَذَابًا مُّهِينًا

Amharic Translation - Africa Academy151. በእውነቱ እነዚያ ከሓዲያን እነርሱው ናቸው:: ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَلَمْ يُفَرِّقُوا۟ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ أُو۟لَٰٓئِكَ سَوْفَ يُؤْتِيهِمْ أُجُورَهُمْ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy152. እነዚያ በአላህና በመልዕክተኞቹ ያመኑ፤ ከእነርሱም መካከል በአንዱም ያልለዩ ሰዎች እነዚያ ምንዳዎቻቸው በእርግጥ ይሰጣቸዋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْـَٔلُكَ أَهْلُ ٱلْكِتَٰبِ أَن تُنَزِّلَ عَلَيْهِمْ كِتَٰبًا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَقَدْ سَأَلُوا۟ مُوسَىٰٓ أَكْبَرَ مِن ذَٰلِكَ فَقَالُوٓا۟ أَرِنَا ٱللَّهَ جَهْرَةً فَأَخَذَتْهُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ بِظُلْمِهِمْ ثُمَّ ٱتَّخَذُوا۟ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَٰتُ فَعَفَوْنَا عَن ذَٰلِكَ وَءَاتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَٰنًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy153. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመጽሐፉ ባለቤቶች እነርሱ ላይ ከሰማይ መጽሐፍን እንድታወርድ ይጠይቁሃል:: ከዚህም የከበደን ጥያቄ ከዚህ በፊት ሙሳን በእርግጥ ጠይቀዋል:: «አላህን በግልጽ አሳየን።» ብለዋል:: በበደላቸዉም ምክንያት መብረቅ ያዘቻቸው:: ከዚያም ተዓምራት ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድረገው ያዙ:: ከዚያ ያንን ይቅር አልን:: ሙሳንም ግልጽ ስልጣን ሰጠነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرَفَعْنَا فَوْقَهُمُ ٱلطُّورَ بِمِيثَٰقِهِمْ وَقُلْنَا لَهُمُ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْبَابَ سُجَّدًا وَقُلْنَا لَهُمْ لَا تَعْدُوا۟ فِى ٱلسَّبْتِ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَٰقًا غَلِيظًا

Amharic Translation - Africa Academy154. በቃል ኪዳናቸው ምክንያት የጡር ተራራን ከበላያቸው አነሳን:: ለእነርሱም «ደጃፍን ስትገቡ አጎንብሳችሁ ግቡ።» አልን:: ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላለፉ።» አልን:: ከእነርሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَٰقَهُمْ وَكُفْرِهِم بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَقَتْلِهِمُ ٱلْأَنۢبِيَآءَ بِغَيْرِ حَقٍّ وَقَوْلِهِمْ قُلُوبُنَا غُلْفٌۢ بَلْ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَيْهَا بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy155. ቃል ኪዳናቸውን በማፍረሳቸው፤ በአላህ አናቅጽ በመካዳቸው፤ ነብያትን ያለ አግባብ በመግደላቸውና «ልቦቻችን ሽፍን ናቸው።» በማለታቸውም ምክንያት ረገምናቸው:: በእውነቱ በክህደታቸው ምክንያት አላህ በእርሷ ላይ አተመ:: ስለዚህ ጥቂትን እንጂ አያምኑም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَبِكُفْرِهِمْ وَقَوْلِهِمْ عَلَىٰ مَرْيَمَ بُهْتَٰنًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy156. በመካዳቸዉም በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን በመናገራቸው ምክንያት ረገምናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا ٱلْمَسِيحَ عِيسَى ٱبْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ ٱللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ وَإِنَّ ٱلَّذِينَ ٱخْتَلَفُوا۟ فِيهِ لَفِى شَكٍّ مِّنْهُ مَا لَهُم بِهِۦ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا ٱتِّبَاعَ ٱلظَّنِّ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًۢا

Amharic Translation - Africa Academy157. «እኛ የአላህ መልዕክተኛ የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳን ገደልን።» በማለታቸውም ረገምናቸው:: አልገደሉትም:: አልሰቀሉትምም:: ግን የተገደለው ሰው ለእነርሱ በዒሳ ተመሰለባቸው:: እነዚያ በእርሱ ጉዳይ የተለያዩት በእርሱ መገደል በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም እርግጠኛ እውቀት የላቸዉም:: በእርግጥም አልገደሉትም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَل رَّفَعَهُ ٱللَّهُ إِلَيْهِ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy158. ይልቁንስ አላህ ወደ እርሱ አነሳው:: አላህም አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِن مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا لَيُؤْمِنَنَّ بِهِۦ قَبْلَ مَوْتِهِۦ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy159. ከመጽሐፉ ባለቤቶች መካከልም ከነብዩ ዒሳ ሞት በፊት በነብዩ ዒሳ በእርግጥ በትክክል የሚያምን እንጂ አንድም የለም:: በትንሳኤ ቀንም ዒሳ በእነርሱ ላይ መስካሪ ይሆናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَبِظُلْمٍ مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ حَرَّمْنَا عَلَيْهِمْ طَيِّبَٰتٍ أُحِلَّتْ لَهُمْ وَبِصَدِّهِمْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ كَثِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy160. ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል በፈጸሙት በደልና ሰዎችን ከአላህ መንገድ በብዙ በመከላከላቸው ምክንያት ለእነርሱ ተፈቅደው የነበሩ ጣፋጮች ምግቦችን እርም አደረግንባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَخْذِهِمُ ٱلرِّبَوٰا۟ وَقَدْ نُهُوا۟ عَنْهُ وَأَكْلِهِمْ أَمْوَٰلَ ٱلنَّاسِ بِٱلْبَٰطِلِ وَأَعْتَدْنَا لِلْكَٰفِرِينَ مِنْهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy161. ከእርሱ በቁርጥ የተከለከሉ ሲሆኑ አራጣን በመያዛቸውና የሰዎችን ገንዘቦች ያለ አግባቡ በመብላታቸዉም ምክንያት የተፈቀደላቸውን እርም አደረግንባቸው:: ከእነርሱም መካከከል ለከሓዲያን አሳማሚ ቅጣት አዘጋጀን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّٰكِنِ ٱلرَّٰسِخُونَ فِى ٱلْعِلْمِ مِنْهُمْ وَٱلْمُؤْمِنُونَ يُؤْمِنُونَ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ وَٱلْمُقِيمِينَ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱلْمُؤْتُونَ ٱلزَّكَوٰةَ وَٱلْمُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ أُو۟لَٰٓئِكَ سَنُؤْتِيهِمْ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy162. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ግን ከእነርሱ ውስጥ በእውቀት የጠለቁት ክፍሎችና ትክክለኛ ምዕመናኖቹ ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊት በተወረደው መጽሐፍ ያምናሉ። ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው ሰጋጆቹ፣ ዘካንም ሰጪዎቹ በአላህና በመጨረሻው ቀንም ትክክለኛ አማኞቹን እነዚያ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጣቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ كَمَآ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ نُوحٍ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ وَٱلْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَٰرُونَ وَسُلَيْمَٰنَ وَءَاتَيْنَا دَاوُۥدَ زَبُورًا

Amharic Translation - Africa Academy163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ ኑህና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነብያት መልዕክታችንን እንዳወረድን ሁሉ ወደ አንተም ቁርኣንን አወረድን:: ወደ ነብዩ ኢብራሂም፤ ወደ ነብዩ ኢስማኢልም፤ ወደ ነብዩ ኢስሃቅም፤ ወደ ነብዩ የዕቆብም፤ ወደ ነገዶችም፤ ወደ ነብዩ ዒሳም፤ ወደ ነብዩ አዩብም፤ ወደ ነብዩ ዩኑስም፤ ወደ ነብዩ ሃሩንና ወደ ነብዩ ሱለይማን አወረድን:: ለነብዩ ዳውድም ዘቡርን ሰጠነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَرُسُلًا قَدْ قَصَصْنَٰهُمْ عَلَيْكَ مِن قَبْلُ وَرُسُلًا لَّمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ وَكَلَّمَ ٱللَّهُ مُوسَىٰ تَكْلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልዕክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውንም መልዕክተኞች እንደላክን ሁሉ አንተን ላክንህ:: አላህ ነብዩ ሙሳንም ማነጋገርን አነጋገረው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رُّسُلًا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةٌۢ بَعْدَ ٱلرُّسُلِ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy165. ከመልዕክተኞች በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ምንም አስረጂ እንዳይኖራቸው አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርገን መልዕክተኞችን ላክን:: አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ ጥበበኛ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّٰكِنِ ٱللَّهُ يَشْهَدُ بِمَآ أَنزَلَ إِلَيْكَ أَنزَلَهُۥ بِعِلْمِهِۦ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَشْهَدُونَ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy166. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ግን ባንተ ላይ ባወረደው ቁርኣን ይመሰክራል:: በእውቀቱ አወረደው:: መላዕክቱም ይመሰክራሉ:: መስካሪነትም በአላህ ብቻ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ قَدْ ضَلُّوا۟ ضَلَٰلًۢا بَعِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy167. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድም ሰዎችን ያገዱ ሰዎች ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳቱ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَظَلَمُوا۟ لَمْ يَكُنِ ٱللَّهُ لِيَغْفِرَ لَهُمْ وَلَا لِيَهْدِيَهُمْ طَرِيقًا

Amharic Translation - Africa Academy168. እነዚያ የካዱና የበደሉ አላህ የሚምራቸውና ቅን መንገድን የሚመራቸው አይደለም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِلَّا طَرِيقَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy169. ግን በውስጧ ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ የገሀነምን መንገድ ይመራቸዋል:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَكُمُ ٱلرَّسُولُ بِٱلْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَـَٔامِنُوا۟ خَيْرًا لَّكُمْ وَإِن تَكْفُرُوا۟ فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy170. እናንተ ሰዎች ሆይ! መልዕክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ:: እናም ባመጣው እመኑ ለእናንተ የተሻለ ይሆናል:: በአላህ ብትክዱም እሱን (ቅንጣት) አትጎዱትም:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًا لَّكُمْ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌ وَٰحِدٌ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy171. እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ:: በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ:: የመርየም ልጅ አል መሲህ ዒሳ የአላህ መልዕክተኛ ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉና ከእርሱ የሆነ መንፈስ ብቻ ነው:: በአላህና በመላዕክተኞቹ እመኑ:: «አማልዕክት ሶስት ናቸው።» አትበሉ:: ተከልከሉ:: ለእናንተ የተሻለ ይሆናልና:: አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው:: ለእርሱም ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: መመኪያነትም በአላህ በቃ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّن يَسْتَنكِفَ ٱلْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ ٱلْمُقَرَّبُونَ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا

Amharic Translation - Africa Academy172. አል መሲህ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፍም:: ቀራቢዎች የሆኑ መላዕክትም እንዲሁ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጸየፉም:: ወደ አላህ እርሱን ከመገዛት የሚጸየፉና የሚኮሩ ሁሉ አላህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضْلِهِۦ وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ٱسْتَنكَفُوا۟ وَٱسْتَكْبَرُوا۟ فَيُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy173. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል:: ከችሮታዉም ይጨምርላቸዋል:: እነዚያን የተጸየፉትና የኮሩትን ግን አሳማሚውን ቅጣት ይቀጣቸዋል:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ዘመድና ረዳት አያገኙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَكُم بُرْهَٰنٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ نُورًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy174. እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥም አስረጅ መጣላችሁ:: ወደ እናንተም ገላጭ የሆነን ብርሃንን (ቁርኣንን) አወረድን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ بِٱللَّهِ وَٱعْتَصَمُوا۟ بِهِۦ فَسَيُدْخِلُهُمْ فِى رَحْمَةٍ مِّنْهُ وَفَضْلٍ وَيَهْدِيهِمْ إِلَيْهِ صِرَٰطًا مُّسْتَقِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy175. እነዚያማ በአላህ ያመኑና በእርሱ የተጠበቁ ሰዎች ከእርሱ በሆነው እዝነትና ችሮታ ውስጥ እርግጥ ያስገባቸዋል:: ወደ እርሱም ቀጥተኛ መንገድን ይመራቸዋልም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَسْتَفْتُونَكَ قُلِ ٱللَّهُ يُفْتِيكُمْ فِى ٱلْكَلَٰلَةِ إِنِ ٱمْرُؤٌا۟ هَلَكَ لَيْسَ لَهُۥ وَلَدٌ وَلَهُۥٓ أُخْتٌ فَلَهَا نِصْفُ مَا تَرَكَ وَهُوَ يَرِثُهَآ إِن لَّمْ يَكُن لَّهَا وَلَدٌ فَإِن كَانَتَا ٱثْنَتَيْنِ فَلَهُمَا ٱلثُّلُثَانِ مِمَّا تَرَكَ وَإِن كَانُوٓا۟ إِخْوَةً رِّجَالًا وَنِسَآءً فَلِلذَّكَرِ مِثْلُ حَظِّ ٱلْأُنثَيَيْنِ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ أَن تَضِلُّوا۟ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۢ

Amharic Translation - Africa Academy176. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይጠይቁሃል: «ወላጆችና ልጅ ሳይኖረው በሚወረስ ሟች ሰው ጉዳይ አላህ ይነግራችኋል።» በላቸው፡፡ ልጅ የሌለው ሰው ቢሞትና ለእርሱ እህት ብትኖረው ለእርሷ ከተወው ንብረት ግማሽ አላት፡፡ እርሱም ለእርሷ ልጅ የሌላት እንደሆነች በሙሉ ይወርሳታል፡፡ ሁለት እህቶች ወይም ከሁለት በላይ ቢሆኑ ግን ከተወው ንብረት ከሶስት ሁለት እጅ አላቸው ፡፡ ወንድሞችና እህቶች ወንዶችና ሴቶች ቢሆኑ ደግሞ ለወንድ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው ፡፡ አላህ እንዳትሳሳቱ ህግጋትን ለእናንተ ያብራራል ፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነውና፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70