وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ أَنِّى قَدْ جِئْتُكُم بِـَٔايَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ أَنِّىٓ أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ ٱلطِّينِ كَهَيْـَٔةِ ٱلطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًۢا بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَأُبْرِئُ ٱلْأَكْمَهَ وَٱلْأَبْرَصَ وَأُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ ٱللَّهِ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِى بُيُوتِكُمْ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
Amharic Translation - Africa Academy49.«ወደ ኢስራኢል ልጆችም መልዕክተኛ ያደርገዋል። ይላልም: ›, ‹እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዐምር መጣሁላችሁ:: እኔ ለእናንተ ከጭቃ የወፍ ቅርጽ አይነት እፈጥራለሁ:: በእርሱም እተነፍስበታለሁ:: ከዚያም በአላህ ፈቃድ ወፍ ይሆናል:: እውር ሆኖ የተወለደንም ለምጸኛንም በአላህ ፈቃድ አድናለሁ:: ሙታንንም በአላህ ፍቃድ አስነሳለሁ:: የምትበሉትንና በየቤቶቻችሁ የምታደልቡትን ሁሉ እነግራችኋለሁ:: (መረጃዎችን አገናዝባችሁ) የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ ግልጽ ተዐምር አለበት።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ (ይላልም)፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡»