caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 119

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:119

هَٰٓأَنتُمْ أُو۟لَآءِ تُحِبُّونَهُمْ وَلَا يُحِبُّونَكُمْ وَتُؤْمِنُونَ بِٱلْكِتَٰبِ كُلِّهِۦ وَإِذَا لَقُوكُمْ قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوْا۟ عَضُّوا۟ عَلَيْكُمُ ٱلْأَنَامِلَ مِنَ ٱلْغَيْظِ قُلْ مُوتُوا۟ بِغَيْظِكُمْ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Amharic Translation - Africa Academy119. እናንተ ትወዷቸዋላችሁ:: እነርሱ ግን በፍጹም አይወዷችሁም:: እናንተ በሁሉም መጽሐፍት ታምናላችሁ:: እነርሱ ግን ባገኟችሁ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ:: ከናንተ ባገለሉ ጊዜ ግን ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጥቆቻቸውን (ጣቶቻቸውን) ይነክሳሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቁጭታችሁ ሙቱ። አላህ ልቦች የቋጠሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነሆ እናንተ እነዚያ የምትወዱዋቸው ናችሁ፡፡ (እነሱ) ግን አይወዱዋችሁም፡፡ በመጽሐፉም በሁሉም ታምናላችሁ፡፡ ባገኙዋችሁም ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ባገለሉም ጊዜ ከቁጭታቸው የተነሳ በእናንተ ላይ ዐጽቆቻቸውን ይነክሳሉ፡፡ «በቁጭታችሁ ሙቱ፤ አላህ ልቦች የቋጠሩትን ዐዋቂ ነውና» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70