caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 195

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:195

فَٱسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّى لَآ أُضِيعُ عَمَلَ عَٰمِلٍ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ بَعْضُكُم مِّنۢ بَعْضٍ فَٱلَّذِينَ هَاجَرُوا۟ وَأُخْرِجُوا۟ مِن دِيَٰرِهِمْ وَأُوذُوا۟ فِى سَبِيلِى وَقَٰتَلُوا۟ وَقُتِلُوا۟ لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ ثَوَابًا مِّنْ عِندِ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسْنُ ٱلثَّوَابِ

Amharic Translation - Africa Academy195. እናም ጌታቸው «እኔ ከናንተ ውስጥ የወንድንም ሆነ የሴትን መልካም ስራ ወሮታ አላጠፋም:: ከፊላችሁ የከፊሉ አካል ነው።» በማለት ልመናቸውን ተቀበላቸው:: እነዚያ ለዲን ሲሉ የተሰደዱ፣ ከአገሮቻቸዉም በግፍ የተባረሩ፣ በመንገዴም (ሁከት የደረሰባቸው)፣ የተጠቁ፣ የተጋደሉ እና የተገደሉም ክፉ ስራዎቻቸውን አብስላቸዋለሁ:: በስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሰባቸውን ገነቶች አስገባቸዋለሁ:: እነርሱም ከአላህ ዘንድ የሆነን ከፍተኛ ምንዳ ይመነዳሉ:: አላህ እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጌታቸውም «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፡፡ እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ »
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70