caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Aal-i-Imraan፣ አንቀጽ 152

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 89 · 3:152

وَلَقَدْ صَدَقَكُمُ ٱللَّهُ وَعْدَهُۥٓ إِذْ تَحُسُّونَهُم بِإِذْنِهِۦ حَتَّىٰٓ إِذَا فَشِلْتُمْ وَتَنَٰزَعْتُمْ فِى ٱلْأَمْرِ وَعَصَيْتُم مِّنۢ بَعْدِ مَآ أَرَىٰكُم مَّا تُحِبُّونَ مِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلدُّنْيَا وَمِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلْـَٔاخِرَةَ ثُمَّ صَرَفَكُمْ عَنْهُمْ لِيَبْتَلِيَكُمْ وَلَقَدْ عَفَا عَنكُمْ وَٱللَّهُ ذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy152. በእርግጥ አላህ በፈቃዱ ጠላቶቻችሁን በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ቃልኪዳንን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ:: የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁም ጊዜ (ግን እርዳታውን ከለከላችሁ):: ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከናንተም ውስጥ የመጨርሻይቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ:: በእርግጥም ለእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ:: አላህ ሁልጊዜም በአማኞች ላይ የችሮታ ባለቤት ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም በፈቃዱ በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ኪዳኑን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ፡፡ የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመጻችሁ ጊዜ (እርዳታውን ከለከላችሁ)፡፡ ከእናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ፡፡ ከእናንተም የመጨረሻይቱን ዓለም የሚሻ አልለ፡፡ ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ፡፡ በእርግጥም ከእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ፡፡ አላህም በምእምናን ላይ የችሮታ ባለቤት ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70