وَٱعْتَصِمُوا۟ بِحَبْلِ ٱللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا۟ وَٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَآءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِۦٓ إِخْوَٰنًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ ٱلنَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy103. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የአላህን ጠንካራ የእምነት ገመድም ሁላችሁም ያዙ:: አትለያዩም። ጠበኞች በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋም አስታውሱ:: ይሀውም በልቦቻችሁ መካከል አስማማ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ:: በእሳት ጉድጓድ አፋፍ ላይ የነበራችሁ ስትሆኑ ከእርሷም አዳናችሁ:: ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አናቅጽን እንደዚሁ ያብራራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየአላህንም (የማመን) ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡