هُوَ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ مِنْهُ ءَايَٰتٌ مُّحْكَمَٰتٌ هُنَّ أُمُّ ٱلْكِتَٰبِ وَأُخَرُ مُتَشَٰبِهَٰتٌ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَٰبَهَ مِنْهُ ٱبْتِغَآءَ ٱلْفِتْنَةِ وَٱبْتِغَآءَ تَأْوِيلِهِۦ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُۥٓ إِلَّا ٱللَّهُ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِى ٱلْعِلْمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ
Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያ ባንተ ላይ መጽሐፍን-(ቁርኣንን) ያወረደ ነው:: ከመጽሐፉም ውስጥ ግልጽ የሆኑ አናቅጽ አሉ:: እነርሱም የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሻሚ ትርጉም ያላቸው አሉ:: እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሌሎችን ለማሳሳት በማሰብና ትርጉሙን በሻቸው ለመለወጥ ሲሉ አሻሚ ትርጉም (ተመሳሳይነት) ያሏቸውን አናቅጽ ብቻ ይከታተላሉ። ትክክለኛ ትርጉማቸውን አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አያውቀዉም:: እነዚያ በእውቀት የጠለቁት ግን «በእርሱ አምነናል። ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው።» ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶች እንጂ አይገሰጽም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አልሉ፡፡ እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም ተመሳሳዮች አልሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡ (ትክክለኛ) ትችቱንም አላህ ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ በዕውቀትም የጠለቁት «በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም፡፡